‹‹የዓለም ዋንጫና የኤፍ.ኤም ጋዜጠኞቻችን ፋውል››
ጥሎብኝ
አሁን አሁን እንደ አሸን የፈሉትን የኤፍ.ኤም ጋዜጠኞች ማዳመጥ አልወድም፡፡ አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ስገባ ካሆነ በስተቀር፤ለምሳሌ
ታክሲ ውስጥ፤ካፌ አልያም ሬድዮንን መዝጋት የማልችልበት ቦታዎች ስሆን ማለቴ ነው፡፡ እናም ከአካውንቲንግ፣ማርኬቲንግ፣ቢዝነስ፣ፊዚክስ፣
ባዮሎጂ ወዘተርፈ የመጡ ስራ አጦች የሚሰባሰቡበት ሞያ እየሆነ ስለመጣም የሬድዮ ጋዜጠኝነት ለአድማጮች የጆሮ ህመም ከሆነ ሰንብቷል፡፡
እናላችሁ
ትላንት በታክሲ እየሄድኩ፣ከሚንኮረኮረው የታክሲው ልሳን የዛሚ 96.3 ሬድዮን ሳዳምጥ የሰማሁትን አሳፋሪና አስቂኝ የጋዜጠኞች የቀጥታ
ወግ ላካፍላችሁ፡፡
አንድ
ወንድና አንዲት እንስት ሆነው ወቅታዊ ወሬዎችን በቀጥታ ስርጭት እየጠረቁ ነው፡፡ ወንዱ ጋዜጠኛም እንዲህ ሲል ጀመረ፡፡
‹‹እንግዲህ
እንትናዬ(የጋዜጠኛዋን ስም በቁልምጫ ጠርቶ) የዓለም ዋንጫ በብራዚል ይካሔዳል›› በማለት ሲጀምር ደነገጥኩ፡፡ እንዴ ዛሬ ስንት
ቀኑ ነው የዓለም ዋንጫ መካሄድ ከተጀመረ? ስል ራሴን ጠየቅኩ፡፡
ጋዜጠኛ በመሰረቱ እንዲህ ያሉ ቀላል መሠረታዊ ስህተቶችን ሲፈፅም
ልቡ ስቱድዮ ውስጥ የለም ማለት ነው፡፡ አልያም በደመ ነፍስ በወረቀት ላይ የጫረውን ሳያርም እያነበበ መሆን አለበት፡፡
‹‹
ወደ 60 ሺህ በላይ ተመልካች የሚይዘው የሳኦ ፓውሎ ስታድየም ብዙ ሺህ ተመልካችን አስተናግዷል›› ሲል በመቀጠል ላይ ከተናገረው
እውነታ ጋር የሚፋለስ ሌላ ጋዜጠኛዊ ፋውል ሰራ፡፡ እኔ ብሆን እስካሁን ይህን ጋዜጠኛ በአንድ ቢጫ እና በሌላ ማስጠንቀቂያ አስደነብረው
ነበር፡፡ ለመሆኑ አዘጋጅ የሌለው ፕሮግራም ይሆን ስል ሳቅ አልኩ፡፡
‹‹አሃ!››
ሴቷ ጋዜጠኛ ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹
ስንት ሚልዮን ማለት ነው የሚይዘው?›› ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳቄን ለቀቅኩት፡፡
‹‹እያወራነው
ያለው እኮ ስለ ስታድየም ነው›› በማለት ሊያርማት ሞከረ፡፡ ሃፍረት በተከናነበው ሳቅ እጅግ የማይገናኙ ነገሮችን በመጨማመር እየቀለደች
እንደሆነ ለማሳየት ሞከረች፡፡ በእኔ ጆሮ እምነት ግን አልተሳካላትም፡፡
ከዛ
በኋላም ተመሳሳይ ስህተቶችን እየደረቡና እየደራረቡ፡፡ ስቱድዮ ከገቡበት ደቂቃ አንስቶ አድማጭን ጋራ እንዳጋቡ ቀጠሉ፡፡ መድረሻዬ
ሆነና እኔም ጆሮዬን ለመታደግ ከታክሲው ወረድኩ፡፡
የሬድዮ
ስቱድዮ ውይይት ጥንቃቄ የሚጠይቅና በምንወያይበት ጉዳይ ዙሪያ ንባብና ሰፊ ዝግጅት የሚጠይቅ እንደሆነ ከጋዜጠኝነት ትምህርትም ሆነ
ልምዴ ተነስቼ እገነዘባለሁ፡፡ እና እነዚህ ጋዜጠኞች እንዴት ይህን መሰል ስህተት እየፈፀሙ ቀጠሉ የሚለው ነገር ቢነሳ አንድም ሞያቸው
አይደለም ወይም ደግሞ ሳይዘጋጁ እየቀባጠሩ መሆን አለበት፡፡ በፍቅር ከሚሰሩ ሞያዎች መካከል አንዱ ጋዜጠኝነት ነው፡፡ ሙያውን ብቻ
መማር በቂ እንዳልሆነ እነ ጳውሎስ ኞኞ በሚገባ አሳይተውናል፡፡ ከአፋችን የሚወጡት ቃላት ማራኪና አድማጭን የሚወክሉ መሆን አለባቸው፡፡
የቃላት አጠቃቀማችን እጅግ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ የምንናገራቸው ነገሮች ደግሞ ለአድማጭ ማንነታችንና ብቃታችንን ያሳብቃሉ፡፡
ለነገሩ
እነዚህን ‹‹ጋዜጠኞች›› ጠቀስኩ እንጂ በመስኮተ ምስሉም (በቲቪ) ሆነ በምራየ ኩነት (በሬድዮ) ብዙ እጅግ ለአድማጭም ሆነ ለተመልካች
የማይመጥኑ ነገሮችንና ንግግሮችን የሚዘረግፉ ሥራ ፈላጊዎች የትየለሌ ናቸው፡፡ ብቻ ኤፍ.ኤም ሬድዮ (ምራየ ኩነት) ጋዜጠኞችን ላለማዳመጥ
የወሰንኩትም ሙያ ሲረጋገጥና ምራየ ኩነቱም የሙያተኛ ያለህ ሲል ማየቱን ስለማልፈልግ ነው፡፡
ለነገሩ የእነ ጳውሎስ ኞኞን ስራዎች ወደኋላ መለስ ብለን በኮመኮምንበት፣የነዳርዮስ
ሞዲ ነጎድጓዳማ ድምፅን ባደነቅንበት፣የነ ነጋሽ መሃመድ ድምፀ መረዋማ ስራዎችን ባዳመጥንበት ጆሮ እንዴት ብለን እነዚህን እንድናዳምጥ
ይፈረድብናል?
wow, i never imagined it before
ReplyDeleteSorry for writing in English for software reasons.
ReplyDeleteLook! Journalism is at stake here. You can see that with the topical issue Samuel Zemicheal. It was the media that told us he is Phd, Medalist, Ass. Prof., ... this and that ...bla bla bla...now it is the media that is disproving that fact. Such erroneous deeds emanates from nothing but our ill way of practicing journalism. Solution , we need to check and double check facts before appearing to audience, listerners, readers, viewers need to comment on facts broadcast or published at least on thier personal facebook and other social networking accounts leaving aside liking and sharing pictures. Thanks Zememe
The only remedy for such problem is to flourish the subject matter:journalism. For me at this level and at this era it's difficult
Delete