Posts

Showing posts from November, 2013

‹ቆንጆ ሴትና ታክሲ›

መቼም የወሬ ትንሽ የለውምና ባለፈው የ‹እንትን› ዕለት የገጠመኝ ነገር የጋዜጣ ወሬ ማሟሻ አደረግኩት… እና ታድያ እናንተስ ለምን ይቅርባችሁ ብዬ እንካችሁ አልኩ፡፡ በታክሲ ተጠቃሚነቴ ያተረፍኩ ነገር ቢኖር መሰለፍ፣ መረገጥ፣መርገጥ፣ መሯሯጥ፣ ማሯሯጥ፣ መገፍተር፣ መገፍተር (አጥብቃችሁ አንብቡልኝ)፣ መገፈታተር፣ መጎሸም፣ መጎሸም( አሁንም አጥብቃችሁ አንብቡልኝ)   መምታት፣ መመታት ከብዙዎቹ በጥቂቱ የማስታውሳቸው ትሩፋቶቼ ናቸው፡፡ በቋንቋ ደረጃስ ቢሆን ዘወትር የምጠቀምባቸውን ቃላት ሀረጋት…እነ ‹ጫፍ ወራጅ አለ ›… መልስ ስጠኝ…. ጥግ ላይ ያዘው…የት ነህ ?...የመሳሰሉትን በደፈናው ልጥቀስላችሁ እንጂ እናንተም ከናንተ የተሰወረ አይደልም ሆኖም ግን በህልሜም ሆነ በቅዠቴ አንስቻቸው ይሆናል ማን ያውቃል…   ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የሚገርመኝ አንዳንዴ የሚገጥመኝ ነገር ነው…   እናላችሁ ታሪኩ እንዲህ ነው ወደ ፈረንሳይ የሚሄድ ታክሲ አራት ኪሎ አግኝቼ ቁች ብያለሁ፡፡ ዛሬ ግፊያ ባለመኖሩ ቅር ያለኝ እመስላለሁ…….ታክሲው እስኪሞላ ድረስ ወደ ውጭ ሳማትር ግን አንዲት ኮረዳና አንድ ጎልማሳ አንገት ለአንገት ተናንቀው (በፍቅር መሆኑ ነው) እኛ ታክሲ ጋር ሲደርሱ እንደፈረንጆቹ አይነት ተሳስመው ተለያዩ…   ሸክም የቀለላት ያህል ዞር ብላ ሳታየው እንኳን አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለች፡፡…የተቀባችው ሽቶ ተንቀሳቃሽ ቤተ መቅደስ አስመስሏታል፤መቼም አዶ ከርቤ ፣አዶ ከርቤ ከሚሸት የጎረምሳ ጫማ ሳይሻል አይቀርም አልኩ ለራሴ… ጎዟችን ተጀመረ፡፡ በረጅም ሌባ ጣትዋ የስልኳን ገፅ እየነካካች ትንሽ ቆይታ ወደ አንዱ ደወለች ‹‹ወዬ የኔ እንትን..›› ‹‹እየመጣሁ ነው››… ‹‹ቂቂቂቂ…›› ‹‹ ኸ ረ ከማንም ጋር አልነበርኩም ..ተኝቼ ነው ያላነሳሁት