ጀርመን፣ሂትለር፣እግርኳስ፣ኤንጌላ ሜርኬል
የዛሬዎቹን
ጀርመናውያንን ሳስብ ከ2ኛው
የአለም ጦርነት በኋላ ድምጻቸውን አጥፍተው
ዓለም ከደረሰበት ደረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ
ጉብ ያሉት ጀርመናውያን ትዝ ይሉኛል፡፡
ሀገራቸውን ‹‹ላንድ ኦፍ አይዲያ›› ሲሉ
ይጠሯታል፡፡ ለነገሩ ምን ያህሎቻችሁ እንደምታውቁ
እርግጠኛ ባልሆንም አብዛኞቹ የሳይንሳዊ
ስልጣኔ ሃሳብ መነሻ ጀርመን ናት፡፡ ዶሽላንድ
ከተበታተነችበት ውድቀት አንድ እስካደረጋት
አጭሩ፣‹‹ጨካኝ›› መሪ ኦቶ ቮን ቢስማርክ
እስከ እኩዩ ሂትለር ድረስም ሆነ ከዛ በኋላ
ጀርመን ለአለም ስልጣኔ ትልቅ አስተዋዕፆ
ነበራት፡፡
የትላንቱን
የጀርመንና የፖርቱጋል እግር ኳስ ፍልሚያ
ስንመለከት፡፡ የሁለት ታላላቅ ሃያላን ሀገራት
ልዮነትን በግልፅ አይተናል፤ፖርቱጋል የኋለኛው
ዘመን፣ጀርመን የዚህኛው፡፡
‹‹ቆራጧ››፣
‹‹ደፋር››፣ ‹‹ብልህ››፣ ‹‹ውሳኔ
የማትፈራ›› አልፎ አልፎም ‹‹አምባገነን››
የሚሏት ኤንጌላ ሜርኬል በፎንቴ ኖቫ ሳልቫዶር
ስታድየም ለጠጥ ብላ ቁጭ እንዳለች በንቃት
የጀመርናውያኑን የኳስ ትርዒት እየተከታተለች
ነው፡፡እንደብዙዎቹ እነስቶች(በተለይ
እንደ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች)
ደማቅና ውድ የሆኑ ልብሶች
የማትወድ እንስት ናት፡፡ እግር ኳስ ብሔራዊ
ፍቅር በሆኑባቸው የአለም ሀገራት እንዲህ
የሚያደርጉ መሪዎች ያሏቸው ከአፍሪካ በስተቀር
ብዙ የአለም መሪዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡
ሆኖም በጀርመናውያን ዘንድ ያልተለመደ ቢመስልም
ኤንጌላ ሜርኬል ግን ከሂትለር በኋላ እስካሁን
ከነበሩት የጀርመን መራሂ መንግስት ለየት
ያለ ባህሪ ያላት ናት፡፡
ይህች
ሴት ስልጣን ላይ ከመጣች በኋላ ጀርመን በምጣኔ
ሃብትና በብዙ ዕድገቶች ተምዘግዝጋለች፡፡
ብዙ ጀርመናውያን እንስቶች በተለያዩ የመንግስት
ቦታዎች ወደ ስልጣን መጥተዋል፤እንደውም
ጀርመን ከሴት ውጭ ባለስልጣን የላትም እንዴ
እስኪባል ድረስ፡፡ ከመጀመርያው በሏ ጋር
ስትለያይ ከቤቱ ፍሪጇን ብቻ ይዛ የወጣችው
የያኔዋ ወጣት፤ሴቶች በማይደፍሩት የሳይንስ
ጥግ በሚሉት በአስትሮ ኬሚስትሪ ትምህርት
የተመረቀችው ያቺ ወጣት፤ዛሬ መሪ ትሆናለች
ብሎ ያሰበም ማንም አልነበረም፡፡
ወደ
ኳሱ እንመለስ፡፡ ጀርመን በሁለት ግብ ፖርቱጋልን
እየመራች ነው፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ የእግር ኳስ
ኮኮቡ ፖርቱጋላዊው ሮናልዶ ላይ አተኩሯል፡፡
ትንታኔዎቹ በእርሱና በእርሱ ላይ ብቻ ያተኮሩ
እስኪመስሉ ድረስም፡፡ለሚዲያ ትኩረት ግድ
የለላቸው ጀርመናውያን እያጠቁ ነው፡፡ በተለይም
በቡድን ስራዎች፡፡ ጀርመኖች ከ2ኛው
የአለም ጦርነት በኋላ ያካበቱት ትልቅ ልምድ
በቡድን መስራት ነው፡፡
ብዙ
ጊዜ ስማቸው የማይታወቅ ነገር ግን ብቁ ተጫዋቾችን
ይዘው በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ይቀርባሉ፡፡
በውበት አልባው የእግር ኳስ አጨዋወታቸው
ለዘመናት ቢታሙም አሁን አሁን ግን ትልቅ ለውጥ
አምጥተዋል፡፡የዘረኝነት ችግር በራሳቸውም
ጭምር ማለትም በምዕራብና ምስራቅ ጀርመናውያን
መካከል አሁንም ድረስ ዘንድ ቢኖርም ከበፊቱ
በተሻለ ከጥቁርና ከምስራቅ አውሮፓ ዝርያ
ያላቸው ተጨዋቾችን አካተዋል፡፡ እንደ ጀርሜን
ቦአቴንግ፣ሳሚ ከዲራ እና ሜሱት ኦዚል ያሉትን
ማለት ነው፡፡
ብዙም
ስለራሱ በማያወራው ጆአኪም ሎዒው የሚመራው
የጀርመን ቡድን ከእረፍት በፊት የቀድሞ የታሪክ
የበላዮቹን ፖርቱጋላውያን 3
ለ0
መርቶ እረፍት ሆነ፡፡
በቀጫጫው ቶማስ ሙለር ግብም ጀርመን ሃያልነቷን
እንዳስጠበቀች እረፍት ሆነ፡፡ ተንኮል የማያጣው
ፖርቱጋላዊው ፔፔ በቀይ የወጣበት የተንኮል
ትርኢት ምስል ከየአቅጣጫው በሚዘንቡ ዘመናዊ
ካሜራዎች ተይዞ የመገናኛ ብዙሃኑን አጥለቀለቀው፡፡
የአዶልፍ
ሂትለር እኩይ ምግባራት ጀርመናውያን ላይ
ትልቅ ጥላ ቢያጠላም እንደ እኔ እምነት ለዛሬዎቹ
ጀርመኖች ጠንካራ መሰረት የሆነ አሻራ ግን
ጥሎ አልፏል ባይ ነኝ፡፡ ጀርመናውያን የበላይነት
ስሜት ባይሰማቸው እንኳን የበላይ ለመሆን
በራቸውን ዘግተው ሲሰሩ ኖረዋል፡፡ እንደ
እውነታውም ዛሬ ላይ አውሮፓን የናጠውን የምጣኔ
ሃብት ቀውስ ማለፍ ችለዋል፡፡ አዶልፍ ሂትለር
በተዘዋዋሪም ቢሆን ጀርመናዊነትና አርያንነት
ለታላቅ ስራ የተዘጋጀ አድርጎ ሕዝቡን ማሳመኑ
ዛሬ ላይ ያለው ጀርመናዊ ምንም እንኳን ኺትለርን
ባያደንቅም በተዘዋዋሪም ቢሆን የበላይ ለመሆን
በሚፈጠሩ ፉክክሮች ውስጥ ሁልጊዜም ጀርመናዊያን
ብቁ ሆነው እንዲዘጋጁ ረድቷቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
ለነገሩ አሁንም ድረስ በግልፅ ባይሆንም
ለሂትለር ታላቅ ፍቅር ያላቸው ጀርመናውያን
እንዳሉ አይካድም፡፡
ሁለተኛው
የጨዋታ ምዕራፍ ተጀመረ፡፡ ጀርመናውያን
በፍፁም የበላይነትና በኳስ ቁጥጥር የቀድሞዋን
የአለም አሳሽና ወራሪ ሃገር ፖርቱጋልን እየመሩ
ነው፡፡ ፖርቱጋላውያን ተስፋ የቆረጡ ይመስላ
፤
አደጋኛ ፋውሎችን በተደጋጋሚ እየሰሩ ነው፡፡
ሚዲያው ላይ በብዛት መታየትና ትኩረት ማግኘት
የሚወደው ኮኮቡ ሮናልዶ ሳይቀር በሆነው ባ
ሆነው
መነጫነጭ ይዟል፡፡ አራተኛውም ጎል ሲገባ
ፖርቱጋላውያን በትክክል እጅ ሰጥተው ነበር፡፡
አሁን ደግሞ ካሜራዎች ሁሉ ወደ ኤንጌላ ሜርኬል
አተኩረዋል፡፡ ሴትየዋም ከጎናቸው ከተቀመጡት
ወዳጃቸው ጋር በተረጋጋ መንፈስ ወግ ላይ
እንደሆኑ በመስኮተ ምስሉ ይታያል፡፡ የመጨረሻውም
ፊሽካ ተነፋ፡፡
ሁሉም
ነገር ለበጎ ነው እንዲሉ ሂትለር የጣለው አሻራ
ወደድንም ጠላንም ለዛሬዋ ጠንካራ ጀርመንና
ጀርመናውያን መሰረት ሆኗል፡፡ ክፉ ሰውም
የበጎ መሰረት መሆን ይችላልና፡፡ እንደኛ
አይነት ታሪክ ላለውና ወድቆ መነሳት ላቃተው
ህዝብም የጀርመናውያን ስንክልክል ጉዞ ትምህርት
ሊሆነን ይገባል፡፡
ጀርመኖች ከ2ኛ ዓለም ጦርነት በኋላ ከምንም ተነስተው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ስለሆኑ እንዳልከው "ክፉ ሰውም የበጎ መሰረት መሆን ይችላል"።ወደ እኛ ስንመጣ ግን ከመተቻቸት ውጪ ከእገሌ የተሻለ ለውጥ አመጣለሁ የሚል እልህ በውስጣችን የለም።ከጀመርመኖች ብዙ ልንማር እንችላለን ባይ ነኝ
ReplyDeleteእውነት ብለሻል፤ ነገር ግን ማን ነው የሚሰማ ነው ጥያቄው
Delete