Posts

Showing posts from April, 2014

ግብረ ሰዶማዊነት፤ሌላኛው ጋሬጣ

Image
                                   በዘመነ ዩሐንስ                                                   ዘመን መፅሔት/2005 ዓ.ም አንዳንድ ጊዜ ባህላችን እና አመለካከታችን በውስጣችን የተፈጥረ ባዕድ ችግር እንዳንፈትሽ ፤ አይነኬ ያልናቸውን ገበናዎቻችን በጉያችን እንደሸሸግን ላናነሳቸው፤ ውግዝ ያልናቸውና ውስጥ ውስጡን ስር እየሰደዱ የመጡ መጤ ችግሮቻችንን አፍረጥርጠን ላናወራባቸው የሕሊና በራችንን እንደከረቸምን የኋላ ኋላ የማንቋቋመው ሲሆንብን ‹ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ› አይነት መፍትሄ ፍለጋ ከረፈደ እንሮጣለን፡፡ ሚስጢራዊ ሕይወታቸው በመሃከላችን መኖራቸውን እንኳን እንዳናስተውል አድርጎናል፡፡ እርስ በእርሳችን በጥርጣሬ ከመተያየት ባለፈ ምንም ማድረግ የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን፡፡ዛሬ ላይ ብልጭ ድርግም በምትል የመገናኛ ብዙሃን ማሳሰቢያ አልፎ አልፎም ቢሆን ሲነገር እንሰማለን፡፡ ሆኖም ጉዳዩ አሳስቦት ወደ መፍትሔ የመጣ፣ ይመለከታኛል የሚል ግለሰብም ሆነ የመንግስት አካል የለም፡፡ ችግሩ ግን አለ ብቻም ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተከታዮቹ እየጨመሩና አያሌ ኢትዮጵያውያን ወደዚህ ድብቅ ማህበረሰብ እየተቀላቀሉ አስፈሪ አደጋ ከፊታችን እንደተጋረጠ ምልክት ሆነውናል፡፡ ራሳቸውን «ዜጋ» እያሉ ይጠራሉ፡፡ ብዙዎቻችን ባለማወቅ የነሱን አለባበስ በመልመዳችን በመሃከላችን መኖራቸውን እንኳን ማወቅ ተስኖናል፡፡ ዝምታችንም ውስጥ ውስጡን እንዲባዙና አዳዲስ መሰል የነሱ አይነት «ዜጋ» እንዲያፈሩ መንገድ ፈጥሮላቸዋል፡፡ ግብረሰዶማውያን በመዲናችን ብቻ ሳይሆን እንደ ሃዋሳ ባሉ ታዳጊ ከተሞች እየበዙና እየተጠናከሩ መምጣታቸው ባህላችን፣ማንነታችና እምነቶቻችንን ሊነቀንቁ