Posts

Showing posts from November, 2014

የአዞ ፍቅር vs የአዞ እንባ

Image
አርባ ምንጭን የረገጠ የትኛውም ጠጉረ ልውጥ ነጭ ሳርንና አዞ እርባታውን ሳያይ እንደማይመለስ አልጠራጠርም፡፡ እኔም እንደማንኛውም ጎብኝ እግሬ ከሄደባቸው ቦታዎች እነዚህ የመጀመርያዎቹ ናቸው ፡፡ እንደው እናንተዬ አርባ ምንጭን በሾርኔ ስሸረምማት ፅዳቷ ሸገርን አፏን ታስይዛት የለ እንዴ ? እርግጠኛ ነኝ አዲስ አበባና አርባ ምንጭ በምዕናብ ቢገናኙ፤ አዲስ አበባ ገና እንዳየቻት ‹ ድሮ ሳውቃት ልጅ ነበረች › እያለች ካሰላሰለች በኋላ ‹‹ እንዴት አባትሽ አምሮብሻል ባክሽ ?!›› ብላ መደነቋ አይቀርም፤ አርባ ምንጭም ድንግጥ ብላ ‹‹ እንዴ ? ምነው እንደዚህ ቦርኮ መሰልሽ አንቺስ ?!›› ብላ መጠየቋ አይቀሬ ነው፡፡ አርባ ምንጭ አዞ እርባታን እንማንኛውም ጎብኜ፤ ጎብኘት፣ ጎብኘት አድርጌ ብወጣም ውስጡ ምን እንደሚመስል እዚህ ላይ ብተርክላችሁ ጊዜ እና ወሬያችሁን ማባከን ነው የሚሆንብኝ፣ ደግሞም የድሮ ጋዜጠኛ የሆንኩ ስለሚመስለኝም እርግፍ አድርጌ ተውኩት ነገር ግን አንድ ልተወው የማልችለው ክስተት ግን ከፍልቅልቅና ተጫዋችዋ አስጎብኚዬ ሰማሁ፡፡   ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ በእርባታ ቦታው ውስጥ ለጎብኚዎች እይታ ከተቀመጡ አዞዎች መካከል ይህ   አዞ የ 26 ዓመት ጎረምሳ ሲሆን ከኋላ ደግሞ የ 23 ዓመት ኮረዳ አዞ ትገኛለች፡፡ እነዚህ አዞዎች በፍቅር ለረጅም ዘመናት አብረው ኖረዋል፤ ብዙ እንቁላሎችንም በአዞ አምሳል ለመፈልፈል በቅተዋል፡፡ በመሃላቸውም አንዳች ፀብ ሳይፈጠር፣አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር አብረው በልተው፣ ውሃቸ