መድሀኒትዎን በ3ዲ እቤትዎ ቁጭ ብለው የሚያዘጋጁበት መሳሪያ.....
ምትሀት የሚመስለው የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ በሁሉም ምዕራባውያን ቤት ውስጥ ሊገባ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀረዋል፡፡ ኮምፒዩተሮች ድሮ ለፕሮግራም አዋቂዎችና ባለሞያዎች ብቻ ነበሩ፤ዛሬ ግን በየሁሉም ቤት ውስጥ መግባት ችለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም አጅብ የሚያሰኙ ግኝቶች ተፈጥረዋል፡፡ አዲሱ ግኝት የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ ተብሎ ይጠራል፡፡ በቤትዎ ሆነውም መድሀኒትዎን እሚያትሙበት እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ ነው፡፡ ከእርስዎ የሚጠበቀው እቤትዎ የሚደርስ ኢንተርኔት እና አዲሱን ከፈረንጆቹ ግንቦት ወር በኋላ ለገበያ የሚቀርበውን የ3ዲ ማተሚያ ማሽን መግዛት ብቻ ነው፡፡ ከዛም የራስዎ ሀኪም ሆኑ ማለት ነው፡፡ እንዴት ይሆናል ብለውስ ጠየቁ? ነገሩ ወዲህ ነው፤ በእስኮትላንድ ግላስኮው ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ በ ሊ ክሮኒን የሚመራ የኬሚስትሪ ምሁራን የምርምር ቡድን ለመድሀኒት መቀመሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎችን ቀመርና 2000 የአሜሪካን ዶላር የሚፈጅ የ3ዲ ማተሚያ ማሽን በመጠቀም አስገራሚ የሆነ ግኝት ፈጥረዋል፡፡ የ3ዲው ማተሚያ በቀላሉ የቤተሙከራ መድሀኒት መቀመሚያ እቃዎችን የሚተኩ ዘመናዊ እቃዎችን በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡ በሚታዘዝበትም ወቅት አስፈላጊውን የመድሀኒቶቹን ውህዶች ይቀምማል፤ በመጨረሻም የሚፈለገውን የኬሚካል ውህድ ፈጥሮ መድሀኒቱን ይሰራል ወይም በዘመነኛው የመሳሪያው አጠራርም መድሀኒቱን ያትማል ማለቱ ይቀላል፡፡ “ኬሚስትሪን ለሁሉም ሰው የማስተዋወቅ ያህል ይሆናል፤ኬሚስትሪ ያን ያህል ከባድ በማይሆንበት ሁኔታ ሰዎች የሳይንስ ፍሬዎችን እንዲጠቀሙ የማድረግ ያህል ነው፡፡” ይላል የግኝቱ ባለቤት ሊ ክሮኒን፡፡ በተለይ ሕክምና በቀላሉ የማይደርስበት አካባቢ ሰዎች የራሳቸውን የራስ ሕመም ክኒን