Posts

Showing posts from January, 2015

ውበትን ፍለጋ

ዛሬ ቁጭ ብዬ የምዕራባውያንን ዜና እየኮመኮምኩ ነው፡፡ አንድም ቢሆን በሚመርጡት የዜና ታሪክ መልዕክቶቻቸው ላይ ከፊትለፊትም ይሁን ከጀርባ ትልቅ ፣ከባድ መልዕክት ያላቸውን ሳያጠኑ፣ሳይመዝኑ በፍፁም እንካችሁ አይሉም፡፡ ምዕራባያን የዜና አውታሮቻቸው ከመድፍና፣ከታንክ የበለጠ አለምን እንደሚደመስሱባቸው ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ሌላው ቢቀር በሕይወት ዘመኔ ካየኋቸው እጅግ ስሜትን ከሚፈትኑ ዘጋቢ ፊልሞች መካከል የቢቢሲ big stories 2014 በሚል የዘጋቢ ፊልሞች ተከታታይ ዝግጅት መካከል ሊሳ ዱሴት (በእድሜ ጠና ያለችው የእንግልጣ ጋዜጠኛ) የሰራችው (#children_of_Syria) አንዱና ብቸኛው ነው ብል ማጋነነን አይሆንብኝም፡፡ የዛን ያህል ደግሞ ለኛ አፍሪካውያን ያላቸው አመለካከት ያናድደኛል ብቻ ሳይሆን ባገኛቸው ራሱ የምለቃቸው አይመስለኝም…አያስቅም..እውነቴን ነው…ዛሬ ያየሁትም ዜና አዘጋጁንም ዘጋቢዋንም ባገኛቸው አርባ ምክር ሊለውጣቸው ስለማይችል አርባ ጅራፍ አዝላቸው ነበር፡፡ ወደ ገደለው እንመለስና የዜናው አውታር አልጀዚራ ነው፤ድንገት ከዜናዎቹ መካከል አንድ አስገራሚ በተለይም ምዕራባውያንም ሆኑ አረቦች በጥቆሮች ላይ ያላቸውን የዘረኝነት አቋም በተዘዋዋሪ የሚያሳይ (ባጭሩ ፈረንጆች በጥቁሮች ላይ ሙድ የሚይዙበት)ዜና ብቅ አለ፡፡ ዜናው ሆን ተብሎ እንደተመረጠ ከዜናው ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡ ‹‹አርቴፊሻል ፀጉር በናይጄሪያውያን ሴቶች ዘንድ ተወዳጅና ገበያው የደራ እየሆነ መጥቷል ›› አለች በናይጄሪያ የአልጀዚራ ዘጋቢዋ ፈገግታ ከፊቷ ሳይጠፋ፡፡ ዞር ዞር ብላ ያነጋገራቸው ሴቶችም የሰጡትን አስተያየት ስሰማ እንደ አፍሪካዊነቴ አፍርሁ፡፡ አንድ ፀጉር ያጠራት ናይጄሪያዊት ወጣት ከህንድና ጃፓን የሚመጡ ጸጉሮችን ለምን እንደምታደርግ ስት