Posts

Showing posts from 2013

‹ቆንጆ ሴትና ታክሲ›

መቼም የወሬ ትንሽ የለውምና ባለፈው የ‹እንትን› ዕለት የገጠመኝ ነገር የጋዜጣ ወሬ ማሟሻ አደረግኩት… እና ታድያ እናንተስ ለምን ይቅርባችሁ ብዬ እንካችሁ አልኩ፡፡ በታክሲ ተጠቃሚነቴ ያተረፍኩ ነገር ቢኖር መሰለፍ፣ መረገጥ፣መርገጥ፣ መሯሯጥ፣ ማሯሯጥ፣ መገፍተር፣ መገፍተር (አጥብቃችሁ አንብቡልኝ)፣ መገፈታተር፣ መጎሸም፣ መጎሸም( አሁንም አጥብቃችሁ አንብቡልኝ)   መምታት፣ መመታት ከብዙዎቹ በጥቂቱ የማስታውሳቸው ትሩፋቶቼ ናቸው፡፡ በቋንቋ ደረጃስ ቢሆን ዘወትር የምጠቀምባቸውን ቃላት ሀረጋት…እነ ‹ጫፍ ወራጅ አለ ›… መልስ ስጠኝ…. ጥግ ላይ ያዘው…የት ነህ ?...የመሳሰሉትን በደፈናው ልጥቀስላችሁ እንጂ እናንተም ከናንተ የተሰወረ አይደልም ሆኖም ግን በህልሜም ሆነ በቅዠቴ አንስቻቸው ይሆናል ማን ያውቃል…   ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የሚገርመኝ አንዳንዴ የሚገጥመኝ ነገር ነው…   እናላችሁ ታሪኩ እንዲህ ነው ወደ ፈረንሳይ የሚሄድ ታክሲ አራት ኪሎ አግኝቼ ቁች ብያለሁ፡፡ ዛሬ ግፊያ ባለመኖሩ ቅር ያለኝ እመስላለሁ…….ታክሲው እስኪሞላ ድረስ ወደ ውጭ ሳማትር ግን አንዲት ኮረዳና አንድ ጎልማሳ አንገት ለአንገት ተናንቀው (በፍቅር መሆኑ ነው) እኛ ታክሲ ጋር ሲደርሱ እንደፈረንጆቹ አይነት ተሳስመው ተለያዩ…   ሸክም የቀለላት ያህል ዞር ብላ ሳታየው እንኳን አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለች፡፡…የተቀባችው ሽቶ ተንቀሳቃሽ ቤተ መቅደስ አስመስሏታል፤መቼም አዶ ከርቤ ፣አዶ ከርቤ ከሚሸት የጎረምሳ ጫማ ሳይሻል አይቀርም አልኩ ለራሴ… ጎዟችን ተጀመረ፡፡ በረጅም ሌባ ጣትዋ የስልኳን ገፅ እየነካካች ትንሽ ቆይታ ወደ አንዱ ደወለች ‹‹ወዬ የኔ እንትን..›› ‹‹እየመጣሁ ነው››… ‹‹ቂቂቂቂ…›› ‹‹ ኸ ረ ከማንም ጋር አልነበርኩም ..ተኝቼ ነው ያላነሳሁት

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ፋርማሲስት ወይዘሪት ዙፋን በቅርብ ጊዜያት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡትን የወሲብ ማነቃቂያ እንክብል ተጠቃሚዎች መብዛት ቢያስገርማትም ምክንያቱን ከብዙዎቹ ተጠቃሚዎች ትሰማለች ነገር ግን ብዙ ጊዜ ያለማዘዣ በድፍረት መጥተው ለመግዛት የሚከራከሩ ተማሪዎችን ስታይ ግን ይበልጠ ቢገርማትም ተማሪዎቹን አስረድታ ከመሸኘት ውጭ ምንም ማድረግ ባለመቻሏ ታዝናለች፡፡ « አንዳንድ ጊዜ እነዚህን ታዳጊዎች ግን የሚቆጣጠራቸው የለም እላለሁ ለራሴ » ትላለች ደግሞ ከዛ የባሰውን ሁኔታ ስታስበው « ዘንድሮ ወላጅም እኮ ተቆጣጣሪ ያስፈልገዋል አሁንማ እነሱም ፋርማሲያችንን የሚያጨናንቁት በዚሁ ቪያግራ ክኒን የተነሳ ነው፡፡ » በማለት አሁን ያለውን ሁኔታ ታስረዳለች፡፡ በአንዳንድ ፋርማሲዎቻችን ውስጥ ያለማንም ከልካይ ይሸጣል፡፡ ገበያ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በመላው ዓለም ላይ ተስፋፍቷል፡፡ በሃገራችን በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ በስፋት ይታወቃል፡፡ የተጠቃሚውም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ የትየለሌ እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔም የሚነገረውን የአደባባይ ምስጢር ልፈትሽ በመነሳሳት ወደ አንዳንድ ፋርማሲዎች ጎራ አልኩ፡፡ በመጀመሪያም ያቀናሁበት ፋርማሲ እጅግ ብዙ ተገልጋይ የሚመላለስበት ቤት ነው፡፡ በቅርብ ያገኘሁትን ፋርማሲስትም ጠጋ ብዬ ቪያግራ መኖሩን ስጠይቀው፣ ‹‹ አዎን የውጩን ነው ወይስ የሃገር ወስጥ ነው የምትፈልገው ?›› ሲለኝ ‹‹ የሃገር ውስጥ›› በፍጥነት መለስኩ ‹‹ ማዘዣ ይዘሃል ?›› ጠየቀኝ ፋርማሲስቱ በትኩረት እየተመለከተኝ ‹‹ አልያዝኩም ግን ደንበኛ ነኝ›› በፈግግታ መለስኩለት፡፡ በጥርጣሬ ዓይን መልከት አድርጎኝ በፍጹም ያለማዘዣ እንደማይሸጥልኝ ቢነግረኝም በሂደት ማሳመን ስለቻልኩም ያለማዘዣ ሊሸጥልኝ ተስማማን፡፡ በሌላኛው

‹‹የኛ ሰው በፌስቡክ››

Image
እንደው እናንተዬ እኔን ብቻ ይሆን የሸተተኝ እናንተንም ጭምር? ‹‹ ስም ከስብ ይሸታል›› ይላሉ አበው፡፡ መለስ አርገው ደግሞ ‹‹መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ›› ይላሉ አይ አበው ለሁሉም ማስረጃ አያጡ!....ስምና ማንነት እጅግ የተነጣጠሉ ነገሮች ቢሆኑም አንዳንዴ ግን ምግባርን ተከትሎ የሚወጡ ስያሜዎች ግን አግባብነት አላቸው፡፡ የማሕበራ ድረ ገፆችን መስፋፋት ተከትሎ እኛም እንደሌሎቹ ህዝቦች መረባችንን ዘርግተን ተጠቃሚ ብንሆንም፡፡ ሁልጊዜም ሀባሻ ያየው ነገር እንዲሉ ስምና ስያሜያችንን ከኩፍስ ማንነታችን ጋር ይዘነው ዘልቀናል፡፡ እናም የኛ ሰው በፌስቡክ የሚቀመው ስምና ማንቆለጳጰሲያ መንገድ እጅግ ግር ም ይለኛል፡፡ የእንስቶቻችን ስያሜ እንደምሳሌ ላንሳውና ‹እከሊት ቆንጆ› ‹እገሊት ስዊት› ‹እንቶኒት ላቭ› ‹እንቶኒት ማር፣ ዲር.... ምናምን የሚሉ ስያሜዎች ራስን ከማንቆለጳጰስ ያለፉም ይመስላሉ አሉላቹ ደግሞ ወንዶቻችን ‹እከሌ ዘማን!› ‹እንቶኔ ዘቤስት!› አልያም ደግሞ ‹እከሌ የተሰኘውን ራፐር ወይም ምዕራባዊ ዘፋኝ ከስሙ ጋር በመቀየጥ የጨበራ ተስካር የመሰለ ስም ይዞ ይመጣልዎታል ድንገት የፌስቡክ ገፅዎን ከፍተው ይሔን ስም ለማንበብ ሲታገሉ ራስዎን ሊያመዎትም ይችላል፡፡ የበለጠ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ ይህን መሰል የተንቆለጳጰሰ ስያሜ ያላቸው ምዕራዉያንም ሆኑ አፍሪካውያን የፌስቡክ እድምተኞች አለማየቴ ነው፡፡ እናም ሀበሾች የተለየ የሚያረገንን የቤት አመል ይዘን እዚሁ ወጣን!?በስነልቦናው ሳይንስ አንድን ማንነት መሆን አለመቻላችን እንድናስመስል የሚያስገድደን የስነልቦና ጉድለት እንዳለ ይጠቅሳል፣ የኛም ችግር ከዚህ የተለየ አይመስለኝም፡፡ እንደውም እዚሁ ፍስቡክ ላይ ያገኘኋት ደስ የምትል አባ

እትዬ የሺና ሳንጃው!

‹‹አዬ የዘለዳው አንተው ሁናቸው እንጂ እነዚህስ እንኳን ሰው መኪናም አይገፋቸው›› አሉ እትዬ የሺ:: ገርበብ ባለው በራቸው ፊት ለፊት እንደ አፈጉባኤ ጉብ እንዳሉ ከፊታቸው የተደረደረውን ሲኒ እና ጀበና ያስተካክላሉ፡፡ አንዴ ከፊታቸው የተሰለፈውን የእጣን ማጨሻ ቆስቆስ ያደርጋሉ፤ አንዴ ደግሞ ከሚንጫጫው ቴሌቪዝናቸው ጋር ለረጅም ደቂቃዎች ይፋጠጣሉ ፡፡ገርበብ ብሎ ከተከፈተው በራቸው ተረክ ባለ ድባብ ወደ ውጭ የሚንቦለቦለው እጣን ደግሞ ማንንም መንገደኛ ይጣራል፡፡ ከእትዬ የሺ በስተሰሜን ባለች በርጩማ ቁጭ ብለው ቡናቸውን ማግ እያደረጉ አይናቸው ን ከቴሌቪዢኑ ሳይነቅሉ ‹‹አ..አቀብለው››…‹‹ ኸረ? ኸረ በለው?...ኤድያ!›› የሚሉት ደግሞ የአቶ ማንተጋፍቶት ባለቤት ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ስማቸው ስለሚጠፋኝ በባለቤታቸው አስታክኬ ነው የምጠራቸው ሁልጊዜም የሚገርመኝ ነገር ተመሳሳይ ሃገራዊ ጉዳይ ሲኖር በተለይም በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ሲኖር የሰፈራችን አሮጊቶች ተሰባስበው ቡናቸውን እየጠጡ ሲከታተሉ ማየት የተለመደ ነው አንዳንድ የሰፈራችን ልጆች ደግሞ እትዬ የሺም ሆኑ እነዚህ ጎረቤቶቻቸው በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳይ በተለይ እግር ኳስና እሩጫ ላይ ያላቸው አቋም መንግስት በጂቲፒው ላይ ካለው አቋም ይስተካከላል ይላሉ፡፡ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከማሊው ስታደ ደ ማሊ ክለብ ጋር የሚያደርገውን ግጥሚያ ደግሞ አንድ ላይ በሕብረት እየተከታተሉ ነው፡፡ ጥሎብኝ እኔ ደግሞ እንዲህ ሕዝብ አይኑን፣ልቡንና ቀልቡን ሰቅሎ የሚይዝ ሃገራዊ ጉዳይ ከመከታተል ይልቅ የሚከታተለውን ወፈሰማይ ሕዝብ ማየት ያዝናናኛል፡፡ ‹‹አዬ እንደው ዛሬስ ብዙ ሳይገባባቸው….›› እትዬ ልኬለሽ መናገር ሲጀምሩ ‹‹ምነው አንቺ ደግሞ፤ ኤጭ አታሟርቺባቸው!›› ቆጣ ብለው መልስ ሰጡ እ

እንደወረደ አንድ ለመንገድ... ከወልቂጤ እስከ ጅማ

ጥሎብኝ አገር ማየት እወዳለሁ፡፡ ይህ አባዜዬም በዚች ትንሽ አገር ላይ ታች ያዞረኛል፡፡መቼም እንደብዙዎቹ ፀሐፍቶች የጉዞ ማስታወሻ የመቀመር ብቃትም ፍላጎትም ባይኖረኝም እግረ መንገዴን ግን የገረመኝን ነገር እንካችሁ ከማለት ወደኋላ አልልም፡፡እና ይህ አባዜዬ ከጓደኞቼ ገንጠል አርጎኝ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ውስጥ ከተተኝ፡፡እስከ ጅማ ድረስም በዚህ መልኩ ልጓዝ ወሰንኩ፡፡ እናላችሁ ጫት እንደባሕር ዛፍ በሚሸመጥጥባት ወልቂጤ ከተማ ስንደርስ መንገደኛው ሁሉ እንደቆሎ ሸጎጥ እያረገ የሚገባው መኪና ይቁጠረውና ዙርባ ዙርባውን የወልቂጤ ጫት ተሸክመው በመስኮት ላይ የሚያፈጡብዎ ትን ንሽ ነጋዴዎች ደንበኞቻቸውን የሚያውቁ ይመስል መንገደኛውን እየለዩ ይጎተጉታሉ፡፡ ወደ ጅማ የሚጓዘው መንገደኛ ሁሉ ያልቃመ ኬላ ላይ ይያዛል የተባለ ይመስል ሁሉም በርብርብ ይገዛል፡፡ የገረመኝ ትዕይንት ደግሞ ዘግየት ብሎ መጣ፡፡ የጅማ እንስቶች ለቂማ ያላቸው ትጋት ፈገግ አሰኘኝ፡፡ እናም ከፊትለፊቴ በሚታየኝ ወገን ቁጭ ያለች አንዲት እመጫት የግራ ጡቷን የልጇ አፍ ውስጥ ሰድራ ቀኝ ጉንጯን ተርዚና እንደወጠረው እያመነዠከች ከወንድ ቃሚ ባልደረቦቿ ጋር በወሬ ትንጫጫለች፡፡ እንግዲህ ልጅም ምርቃናው በናት ጡት ወተት መልክ እንደሚደርሰው እያሰብኩ በፈገግታ ዙርያ ገባን መቃኘት ቀጠልኩ፡፡ ከሰዓታት በኋላ... ወፈ ቃሚ በሙሉ ቡዝዝ ባለ ዓይን ከፊት ለፊቱ የሚመዘዘውን መንገድ እየተመለከተና ከፊት ለፊቱ የሚምዘገዘገውን የጊቤ በረሃ እየገላመጠ፤ያለ አግባብ ባዱ አፉን እያላመጠ፣እያኘከ በምርቃና ቁዘማ ውስጥ በፀጥታ ተቀምጧል፡፡ የመረቀነውን ካልመረቀነው መለየት የሚቻለውም በፈጠጡና በቦዘዙ ዓይኖች መጠን ሳይሆን አይቀርም መሰለኝ የአንዳንዱ አይን ከሽፋሽፍቱ ወጥቶ በመኪና

.............. ............................... «10 በ90»................................

በጥዋት ቢሮዬ ኩርምት ያደረገኝ ብርድ ጋዜጣ ከማንበብ ግን አላገደኝም፡፡ እናም የዛሬውን አዲስ ዘመን እንደነገሩ አለፍ እያልኩ ስመለከት አንድ ዜና ትኩረቴን ሳበው... እንዲህም ይል ነበር « የ10 በ90 የቤት ተመዝጋቢዎች በሙሉ በያዝነው የበጀት አመት ቤት ያገኛሉ» ይላል «ከምራቸውን ነው እነዚህ ሰዎች?» ራሴን ጠየኩት « እኔ እንጃ!?» ሌላኛም እራሴ መለሰልኝ እናላችሁ ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳነብ 10 በ90 የተመዘገበው ህዝብ 23 ሺህ እንደማይበልጥና መንግስት ደግሞ24 ቤቶች እንደገነባ ወይም ገብቶ ሊጨርስ እንደሆነ ያትታል፡፡ እውነት ይህ ከሆነ የሚቀጥለው አመት የሚንበሸበሸው ከተሜ ታየኝ ግን ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ 10በ90 ሲነሳ ሁሌም አብሮ የሚነሳው የቤቱ ጥራት ነው፡፡ ያኔ ለምዝገባ ስንራወጥ ሁለት ጓደኛሞች ድንገት ተገናኝተው ሲጨዋወቱ ትኩረቴን ሳቡት «10በ90 ነህ?» አንደኛው ጠየቀ « አይደለሁም አለማየሁ ነኝ?» ሳቅ በሳቅ «ባክህ አትቀልድ » «አዎ ምንነው?» ለመስማት ጓጓ « ቤቱ ምን እንደሚመስል አይተኸዋል ግን?» « እሱንስ ተወው 10 ፐርሰንት ከፍሎ ቪላ የሚጠብቅ የለም፣ ግን የተመቸኝ ለ10በ90 የተሰጠው ስያሜ ነው» «ማን አሉት ደግሞ?» ፈገግ ለማለት እየተዘጋጀ «ወህኒ ቤት» ድጋሚ ሳቅ በሳቅ «አንዳንዶቹ ደግሞ ደሃ ማቆር» ይሉታል ለምንድን ነው እንደዛ የተባለው?» በመገረም ጠየቀው በድጋሚ « ዲዛይኑን ብታየው ቃሊቲን ያስታውስሃል፣ በቃ ቀጥ ብሎ መደዳውን በሮች ተደርድረውበታል» ወሪያቸው ቢመቸኝም ጥያቸው ልሄድ ተገደደኩ ከዚህ ቀደም እንደተባለውም 10 በ90 ከከተማ ወጣ ባሉ ቦታዎች የሚሰሩ ቤቶች ናቸው ይህ ደግሞ መሃል ከተማ ከሚሰሩት 40 በ60 በጥራትም በተፈላጊነትም ልዩነት እንዳላቸው

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

Image
  ፋርማሲስት ወይዘሪት ዙፋን በቅርብ ጊዜያት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡትን የወሲብ ማነቃቂያ እንክብል ተጠቃሚዎች መብዛት ቢያስገርማትም ምክንያቱን ከብዙዎቹ ተጠቃሚዎች ትሰማለች ነገር ግን ብዙ ጊዜ ያለማዘዣ በድፍረት መጥተው ለመግዛት የሚከራከሩ ተማሪዎችን ስታይ ግን ይበልጠ ቢገርማትም ተማሪዎቹን አስረድታ ከመሸኘት ውጭ ምንም ማድረግ ባለመቻሏ ታዝናለች፡፡ « አንዳንድ ጊዜ እነዚህን ታዳጊዎች ግን የሚቆጣጠራቸው የለም እላለሁ ለራሴ » ትላለች ደግሞ ከዛ የባሰውን ሁኔታ ስታስበው « ዘንድሮ ወላጅም እኮ ተቆጣጣሪ ያስፈልገዋል አሁንማ እነሱም ፋርማሲያችንን የሚያጨናንቁት በዚሁ ቪያግራ ክኒን የተነሳ ነው፡፡ » በማለት አሁን ያለውን ሁኔታ ታስረዳለች፡፡ በአንዳንድ ፋርማሲዎቻችን ውስጥ ያለማንም ከልካይ ይሸጣል፡፡ ገበያ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በመላው ዓለም ላይ ተስፋፍቷል፡፡ በሃገራችን በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ በስፋት ይታወቃል፡፡ የተጠቃሚውም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ የትየለሌ እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔም የሚነገረውን የአደባባይ ምስጢር ልፈትሽ በመነሳሳት ወደ አንዳንድ ፋርማሲዎች ጎራ አልኩ፡፡ በመጀመሪያም ያቀናሁበት ፋርማሲ እጅግ ብዙ ተገልጋይ የሚመላለስበት ቤት ነው፡፡ በቅርብ ያገኘሁትን ፋርማሲስትም ጠጋ ብዬ ቪያግራ መኖሩን ስጠይቀው፣ ‹‹ አዎን የውጩን ነው ወይስ የሃገር ወስጥ ነው የምትፈልገው ?›› ሲለኝ ‹‹ የሃገር ውስጥ›› በፍጥነት መለስኩ ‹‹ ማዘዣ ይዘሃል ?›› ጠየቀኝ ፋርማሲስቱ በትኩረት እየተመለከተኝ ‹‹ አልያዝኩም ግን ደንበኛ ነኝ›› በፈግግታ መለስኩለት፡፡ በጥርጣሬ ዓይን መልከት አድርጎኝ በፍጹም ያለማዘዣ እንደማይሸጥልኝ ቢነግረኝም በሂደት ማሳመን ስለቻልኩም ያለማዘዣ ሊሸጥልኝ ተስማማን፡፡ በ