Posts

Showing posts from 2015

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

በ2014 40 በመቶ አውሮፓውያን ብቻቸውን ይኖራሉ፣ በ2018 በዓለም ላይ ዕድሜያቸው 30 የገቡ ግለሰቦች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት የቤተሰብ ጥገኛ ይሆናሉ በ2019 ማሕበራዊ ድረገፆች ሁሉንም የዓለም ወጣት ላይ ተፅኗቸው ያርፋል፣ በ2026 በዓለም ላይ የግለኝነት ሕይወትን የሚመርጡ ወጣቶች ቁጥር ብቻ 20 በመቶ ይደርሳል፣ በ2038 ላጤዎች በአማካኝ በአንድ አገር ውስጥ ከፍተኛውን የጤና እና የአእምሮ ቀውስ ተጠቂነት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ዱክ ዩኒቨርሲቲ-2012(እ.ኤ.አ) እንደ መግቢያ ያስቀመጥኩት ጥናታዊ መላምት በቅርብ ጊዜ የተሰራ የምዕራባውያን ትንበያ ነው፡፡ እንደ መነሻነት  ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለመመልከት ይጠቅማል ያሉ ተመራማሪዎች የዓለም ሕዝብ አይኑን እንዲገልጥ ሲሉ ይፋ ያደረጉት ጥናትም ነው፡፡ የወንደ ላጤና የሴተ ላጤው ቁጥር በዓለም ላይ መጨመሩ ያሳሰባቸው የዱክ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስጋታቸውን ያሳዩበትም ሰንጠረዥ ነው፡፡ እያንዳንዱ ጋብቻ ወደፍቺ የማምራት ዕድሉ ከጊዜ አንጻር እየጨመረ በመምጣቱም በብቸኝነት በሽታ የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥርን እንደሚጨምረውም ያስረዳሉ፡፡ እስኪ ዛሬ በጥያቄ ልጀምር፡፡ ጥያቄዬን ለራሳችሁ ምላሽ ሰጥታችሁ ተከተሉኝም፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያችን ምን ያህሎቻችን በትዳር፣አልያም ከወላጆቻችን ጋር፣ወይም በተቃራኒው ብቻችንን እየኖርን ነው ብላችሁ ትገምታላችሁ? ምን ያህል ብቻችንን ውለን ብቻችንን ማደርን እንችላለንስ? ብቸኝነታችን ምን አሳጥቶታናል፣ምንስ እንድናገኝ ረድቶናል? እነዚህን ጥያቄዎች እንደ ግለሰብ መጀመሪያ መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ ወንደላጤ አልያም ሴተ ላጤ ከሆኑ በመቀጠልም

ሰላማዊ እንቅልፍን ይሻሉ?

እንግዲያውስ የእንቅልፍዎ ጠንሳሽ ሆርሞኖችን ባህሪያት ሊያውቁ ይገባል ሜዲካል መፅሔት መስከረም 2008   ሰው ሆኖ የማይተኛ የለም፡፡  መተኛት ስል እንቅልፍ ብቻ መሆኑን እንዲታሰብልኝ፤ እንሰሳም ሆኖ እንደዛው፤የተለየ አፈጠጣር ካላቸው በስተቀር፡፡ እንቅልፍ ለሰው ልጅ አካላዊ ዑደት ወሳኝ ተፈጥሯዊ ክሰተት መሆኑ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሳይንስ ስለእንቅልፍ የሚረዳው እውነታ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ቢመጣም እስካሁን ያልተመለሱ አያሌ ጥያቄዎች አሁንም እንዳሉ ናቸው፡፡ እንቅልፍና ሕልምን የሚያያይዘው ምስጢር ደግሞ ዋነኛው ነው፡፡ ለምን እንደምናልም ዛሬ ድረስ ግልፅ መልስ የለም፡፡ ሕልም ትርጉም አልባ ወይስ በሕይወታችን ውስጥ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ይሆን የሚለውም ጥያቄ እንዲሁ እንቆቅልሽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንቅልፍ በሕይወታችን ውስጥ ስላለው ወሳኝ ድርሻ ሳይንስ ብዙ የሚለን ይኖራል፡፡ እንቅልፍና የሰው ልጅ አካላዊ ንቃት፤ሥራ እና አጠቃላይ ኡደት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ እንቅልፍን የሚያህል ታላቅ የጡዘት ምስጢር የሚጠነስሱ አካላዊ ሆርሞኖች ደግሞ ሌሎቹ ባለሚናዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሆርሞኖችን ማወቅ መረዳትና የሚጠብቁብንን መፈፀም በአግባቡ ለመተኛትና ጤነኛ ውጤታማ ሕይወት ለመምራት የሚያስችለንን ስንቅ እንደያዝን ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ በሰውነታችን ያሉ ሆሮሞኖች በአጠቃላይ የሰውነታችንን የሥራ ክንዋኔ የሚቆጣጠሩና የሚፈፅሙ ናቸው፡፡ በአጭሩ ኬሚካላዊ መልዕክት ልንላቸው እንችላለን፡፡ወደ አንድ የሰውነታችን ክፍል አልያም ሕዋስ የሚልኩት የኬሚካል መልዕክት ጠብ አይልም፡፡በተፈለገው ጊዜ ውስጥ ይፈፀማል፡፡ በአብዛኛው በእኛነታችን ላይ ሃያልነት አላቸው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደሚገለፀውም፤በእድገታችን፤በሜታቦሊዝም ስርዓታችን፤

Elusive creative genius

ስለቃሉ የቀረበ ትርጓሜ ምን ማለት እንደምችል ባላውቅም እንደ ርዕስ የተጠቀምኩት ቃል ‹‹ቅዠታዊ ልህቅና›› ከምንለው የአእምሮ ብቃት ጋር አንድነት አለው፡፡ እንዲህ ያሉ ቅዠታም ግን ባለ ልዕለ ሃያል አእምሮ ባለቤቶችና የፈጠራ ሥራ ልሂቃን መኖራቸውን ሳይንስ በየጊዜው ይነግረናል፡፡ በእርግጥ እንዲህ ያሉ ሰዎች በሁሉም ሞያ ቢኖሩም በኪነጥበቡ ውስጥ ያሉት ግን ለየት ይላሉ ይለናል ኒውሮ ሳይንስ፡፡ ነገሩን ወደራሴው ሞያ ፀሐፍትነት ለውሰደውና፤ሁሉም ሰው ፀሐፍት መሆን ይችላል፡፡ ሁሉም ሰው ደራሲ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድን ጥበበኛ ከሌላ የሚለየው ግን የተሰጥኦው ውጤት ነው፡፡ ይህ ተሰጥኦ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ይመስላል፡፡ እነዚህ ጥቂቶች ደግሞ ቅዠታዊ ልህቅናን የተጎናፀፉ ይሏቸዋል፡፡ ከታሪክ መዝገብ ሲመነዘር ጥንታዊ ሮማውያንና ግሪካውያን ፀሐፍት አንዳች መንፈስ ያረፈባቸው ናቸው ይባላሉ፡፡ እነዚህ ፀሐፍት ከተራው ጸሐፍት ይለያሉ፤ሶቅራጠስ ራሱ ሳይቀር ‹‹ዲመን›› ‹‹አንዳች መንፈስ ››በላዬ ላይ ሆኖ በል በል ሲለኝ ሃሳቦቼን አፈልቃለሁ፡፡ እነዚህ ሃሳቦቼ ደግሞ ከሌላው ግዜ የተለዩ ናቸው፡፡ ጠብ እንኳን አይሉም›› ብሏል፡፡ ለነገሩ እኚህ ታላላቅ ፀሐፍት እንደ ተራው ፀሐፍት በየጊዜው ለምን አይፅፉም፤እንደ ዳኛቸው ያሉ ፀሐፍት ለምን በየጊዜው በአደፍርስ አያጠምቁንም? እነ ሐዲስ አለማየሁ ሁልጊዜ ያን የመሰለ ነገር መፃፍ ለምን አቃታቸውስ? ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ የጥበብ ሰዓታት ‹‹moments of creativity›› ዝም ብሎ እንደውሃ ዥረት አይመጣም፡፡ ያቺ ሰዓት መቼ እንደሆነች ጥቂት ጥበበኞች ያውቋታል፡፡ አንዳንድ ልሒቃን ሲጋራውን ሲያቦኑ፣በመጠጥ ጠርሙስ ውስጥ ሲንቦራጨቁ፣ሲቅሙ አልያም ፅፁን ሲጋቱ ድንገት የፈጠራ ሥራ ፍልቅ ትልላቸዋለች፡፡

ባልና ሚስት

ችግር ቁምነገራችን ነው፡፡ ድህነት ልብሳችን ነው፡፡ ልጅነት ደግሞ የድህነት ዘባተሎን የሰበሰበ የቁምነገር ኮሮጇችን ነው፡፡ ልጅነቴን ካደመቁልኝ ታላላቅ ችግሮች መካከል በቤት እጦት ከሰፈር ሰፈር መጦዛችን ነው፡፡ ተወልጄ ለአቅመ መዋዕለ ሕፃናት አልፎም እስከ ሦስተኛ ክፍል ዕድሜዬ ሕይወትን ያሟሸሁባት በመሆኗ እጅግ እወዳታለሁ፡፡ ውቤ በረሃ፤ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ የነ ካሳ ገላግሌ ሰፈር፡፡ ጣፋጭ ትዝታዎችን በአምቦቀቅላ አእምሮዬ ሸክፌ የወጣሁባት ሰፈር ናትና ‹‹ ያን ሰፈር ግን ለምን ለቀቅን ?›› እል ነበር በልጅነት የቁጭት ስሜት …‹‹ ኸረ እንኳን ለቀቅን፤ቤት አልባ እንሆን አልነበር ?›› እላለሁ ዛሬ በበሰለው ሕሊናዬ፡፡ ከእኩዮቼ የሰፈራችን ልጆች ተነጥዬ የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ በመሆኔም የተሻለ የትምህርት ዕድል የተፈጠረለት ሕፃን ( ስኮላርሽፕ ) ያገኘ ተብዬ እቆጠር ነበር፡፡ ቂቂቂ … በነገራችን ላይ ለዚህ ጥረታቸው ወላጆቼን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ዛሬስ እሱ ውለታውን ይክፈላቸው እንጂ እኔማ የኮንዶም ለምኔ .. ይቅርታ የኮንዶሚኒየሜን እንኳን ለባንክ ማጉረስ አልቻልኩም፡፡ ከትዝታ ማህደሬ ውስጥ መዘዝ አድርጌ አንድ አሮጌ የትዝታ ዶሴ እንካችሁ ልበላችሁ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን በሰፈራችን ሜዳ … ( ይግረማችሁ ውቤ በረሃ ያኔ ሜዳ ነበራት .. ለዛውም የኛ ሰፈር ሳይቆጠር እንጢቅ ነዋ !)... እቃ እቃ፤ባልና ሚስት ልንጫወት ተሰባስበናል፡፡ የሙሸሮች ዳስ ተዘጋጀ፡፡የጭቃ ኬክ ተሰናዳ፡፡ እን