ጥያቄ አለኝ
በእውነቱ ወንደኝነት ያጠቃናል፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ‹‹ወንደኝነት››የሚል የአማርኛ የቃል አረባብ ባይኖርም፤ያራባሁት እኔው ነኝ፡፡በቤተ ሙከራዬ፡፡ አብዛኞቹ የአማርኛ ቃላት አላግባብ ፀሐይ ላይ በመዋላቸው የተነሳ ያልባከነ ቃል ስላጠረኝ እንደሆነ ብቻ ተረዱልኝ፡፡ በእውነቱ እኛ ወንዶችም ሆንን አንዳንድ ሴቶች ወንደኝነት(ፆተኝነት) ያጠቃናል፡፡ ለምን ብትሉኝ፤እህ ብትሉኝ አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ስንቶቻችን ነን የሴት አያቶቻችንን ስም የምናውቅ?ባባት በሚጠራ ማህበረሰብ ውስጥ እስኪ የአያቶችህን ስም ጥራ/ጥሪ ብንባል… ‹‹ጉልማ፣ዳንዴው-ዳንዴው፣ሃይሌ-ሃይሌ-ሴሬቦ…›› በቃ ወንድ አያቶቻችን ብቻ፤ ሴት አያቶቻችንንስ? የእናትህ እናትስ? የአባትህ እናትስ? በሴት አያቶቼ ስም እምላለሁ ከአንድ በላይ የእናቱንና የአባቱን እናት፣እናት፣የእናት እናት፣የእናት እናት እ ናት የሚያውቅ ካለ እኔ እቀጣለሁ፡፡ ታላላቅ ስብዕናን የተጎናፀፉ ሴት አያቶቻችን እንደዋዛ ስማቸው ይጠፋል፡፡ በእውነቱ ወንደኝነት ያጠቃናል፡፡ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በወንድ የበላይነት የምትጦዘው ዓለም የሰው ልጅ ወንደኝነት የሚያጠቃው ብቸኛ እንሰሳ ይመስላል፡፡ለምን ብትሉ ይኄ በአንዳንድ እንሰሳት አይሠራማ!፡፡ ለምሳሌ በማህበረጅብ ዋነኛ መሬ ሴት ጅብ ናት፡፡ ወንድ ጅብ የበይ ተመልካች ነው፡፡ ጅብ እንኳን በእንስቶች ይመራል! ይህንንስ ምን ያህሎቻችን እናውቃለን? አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ ከዛሬ 10ሺህ ዓመታት በፊት እነ ግሪክ ሳይሰለጥኑ የነበረው የሰው ልጅ ታሪክ ነው፡፡የዛሬን አያርገውና አለም ያኔ በሴቶች ትመራ ነበር፡፡ ቢቢሲ እንኳን ተደንቆ ይህን ታሪክ <<When God was a woman>> ሲል ተርኮታል፡፡ የዛሬን አያርገውና አለም ያኔ በሴቶች ስት