2012 የማያ ቀን አቆጣጠር መጨረሻ ብቻ ወይስ የአለም ፍፃሜ?
- የማያ ቀን አቆጣጠር በመጪው ዲሴምበር፣21 2012 ያበቃል - ይህን ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል የሚሉ ወገኖች ተበራክዋል - የናሳ ተመራማሪዎች ይህን ውድቅ የሚያደርግ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል፡፡ - የማያ ሕዝቦች የታያቸው የናሳ ተመራማሪዎች ያላዩት ምስጢር ይኖር ይሆን ? - በእርግጥ ከምድር ጋር የምትጋጭ ድብቅ ፕላኔት ትኖር ይሁን ? - በቅርቡ በፀሐይ ላይ የታየው ድንገተኛ ክስተት የትንቢቱ ምልክት እንደተባለው ይሆን? ዘንድሮ በጉጉት ከሚጠበቁ ነገሮች መሀል የፈረንጆቹ ዲሴምበር 21 2012 ቀን ነው፡፡ የጉጉቱ ዋነኛ ምክንያትም የማያን የቀን አቆጣጠር ሰንጠረዥ ማለቅ ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል ተብሎ የተደረገውን ትንቢት ውጤት ምን አንደሚመስል ለማወቅ ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ብሎ ብዙ ጊዜ ሰዎች ያለም ፍፃሜ ይሆናል በማለት አሳዛኝም አስቂም ክስተቶች ተፈፅሞባቸዋል በራሳቸውም ላይ ሲፈፅሙ ታይቷል፡፡የአለም ፍፃሜን በተመለከተ ታላላቅ ቅዱስ መፃህፍትም ሆኑ ሳይንስ ከሚተነብዩት ውጭ የተደረጉ ትንቢቶችና ሙከራዎች የአለምን ሕዝብ ግራ እንዳጋቡ ቆይተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም የአለም ፍፃሜ እንደደረሰ የተነበዩ፤ እራሳቸውን ጨምሮ አያሌ ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደ ሞት ያመሩ ብዙ ግለሰቦችም ባለፉት ጥቂት አመታት ታይተዋል፡፡ ከአለማችን ቀደምት ስልጣኔዎች መሀል አንዱ የሆነው የማያ ሕዝቦች ስልጣኔ የራሱ የቀን አቆጣጠር አለው፡፡ ይህ የቀን አቆጣጠር እንዳጋጣሚ ሆኖም ይሆን ታስቦበት በመጪው የፈረንጆቹ ዲሴምበር ወር ላይ ያበቃል፡፡ ይህን ተከትሎ ማያዎች ከተነበዩት አንዳንድ ትንቢቶች በመነሳት የአለም ፍፃሜ ሊሆን እንደሚችል