Posts

Showing posts from March, 2015

ባልና ሚስት

ችግር ቁምነገራችን ነው፡፡ ድህነት ልብሳችን ነው፡፡ ልጅነት ደግሞ የድህነት ዘባተሎን የሰበሰበ የቁምነገር ኮሮጇችን ነው፡፡ ልጅነቴን ካደመቁልኝ ታላላቅ ችግሮች መካከል በቤት እጦት ከሰፈር ሰፈር መጦዛችን ነው፡፡ ተወልጄ ለአቅመ መዋዕለ ሕፃናት አልፎም እስከ ሦስተኛ ክፍል ዕድሜዬ ሕይወትን ያሟሸሁባት በመሆኗ እጅግ እወዳታለሁ፡፡ ውቤ በረሃ፤ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ የነ ካሳ ገላግሌ ሰፈር፡፡ ጣፋጭ ትዝታዎችን በአምቦቀቅላ አእምሮዬ ሸክፌ የወጣሁባት ሰፈር ናትና ‹‹ ያን ሰፈር ግን ለምን ለቀቅን ?›› እል ነበር በልጅነት የቁጭት ስሜት …‹‹ ኸረ እንኳን ለቀቅን፤ቤት አልባ እንሆን አልነበር ?›› እላለሁ ዛሬ በበሰለው ሕሊናዬ፡፡ ከእኩዮቼ የሰፈራችን ልጆች ተነጥዬ የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ በመሆኔም የተሻለ የትምህርት ዕድል የተፈጠረለት ሕፃን ( ስኮላርሽፕ ) ያገኘ ተብዬ እቆጠር ነበር፡፡ ቂቂቂ … በነገራችን ላይ ለዚህ ጥረታቸው ወላጆቼን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ዛሬስ እሱ ውለታውን ይክፈላቸው እንጂ እኔማ የኮንዶም ለምኔ .. ይቅርታ የኮንዶሚኒየሜን እንኳን ለባንክ ማጉረስ አልቻልኩም፡፡ ከትዝታ ማህደሬ ውስጥ መዘዝ አድርጌ አንድ አሮጌ የትዝታ ዶሴ እንካችሁ ልበላችሁ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን በሰፈራችን ሜዳ … ( ይግረማችሁ ውቤ በረሃ ያኔ ሜዳ ነበራት .. ለዛውም የኛ ሰፈር ሳይቆጠር እንጢቅ ነዋ !)... እቃ እቃ፤ባልና ሚስት ልንጫወት ተሰባስበናል፡፡ የሙሸሮች ዳስ ተዘጋጀ፡፡የጭቃ ኬክ ተሰናዳ፡፡ እን