Posts

Showing posts from November, 2012

2012 የማያ ቀን አቆጣጠር መጨረሻ ብቻ ወይስ የአለም ፍፃሜ?

Image
-          የማያ ቀን አቆጣጠር በመጪው ዲሴምበር፣21 2012 ያበቃል -          ይህን ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል የሚሉ ወገኖች ተበራክዋል -          የናሳ ተመራማሪዎች ይህን ውድቅ የሚያደርግ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል፡፡ -          የማያ ሕዝቦች የታያቸው የናሳ ተመራማሪዎች ያላዩት ምስጢር ይኖር ይሆን ? -          በእርግጥ ከምድር ጋር የምትጋጭ ድብቅ ፕላኔት ትኖር ይሁን ? -          በቅርቡ በፀሐይ ላይ የታየው ድንገተኛ ክስተት የትንቢቱ ምልክት እንደተባለው ይሆን?          ዘንድሮ በጉጉት ከሚጠበቁ ነገሮች መሀል የፈረንጆቹ ዲሴምበር 21 2012 ቀን ነው፡፡ የጉጉቱ ዋነኛ ምክንያትም የማያን የቀን አቆጣጠር ሰንጠረዥ ማለቅ ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል ተብሎ የተደረገውን ትንቢት ውጤት ምን አንደሚመስል ለማወቅ ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ብሎ ብዙ ጊዜ ሰዎች ያለም ፍፃሜ ይሆናል በማለት አሳዛኝም አስቂም ክስተቶች ተፈፅሞባቸዋል በራሳቸውም ላይ ሲፈፅሙ ታይቷል፡፡የአለም ፍፃሜን በተመለከተ ታላላቅ ቅዱስ መፃህፍትም ሆኑ ሳይንስ ከሚተነብዩት ውጭ የተደረጉ ትንቢቶችና ሙከራዎች የአለምን ሕዝብ ግራ እንዳጋቡ ቆይተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም የአለም ፍፃሜ እንደደረሰ የተነበዩ፤ እራሳቸውን ጨምሮ አያሌ ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደ ሞት ያመሩ ብዙ ግለሰቦችም ባለፉት ጥቂት አመታት ታይተዋል፡፡ ከአለማችን ቀደምት ስልጣኔዎች መሀል አንዱ የሆነው የማያ ሕዝቦች ስልጣኔ የራሱ የቀን አቆጣጠር አለው፡፡ ይህ የቀን አቆጣጠር እንዳጋጣሚ ሆኖም ይሆን ታስቦበት በመጪው የፈረንጆቹ ዲሴምበር ወር ላይ ያበቃል፡፡ ይህን ተከትሎ ማያዎች ከተነበዩት አንዳንድ ትንቢቶች በመነሳት የአለም ፍፃሜ ሊሆን እንደሚችል

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?

Image
ሜዲካል ጋዜጣ ሳይንስ ፌቸር     በዘመነ ዮሐንስ ራሰ በራ ነዎት? ወይስ ራሰ በራ ሰው በቤትዎ አለ? እርስዎስ ፀጉርዎ ገባ ገባ፤ሸሸት ሸሸት ማለት ጀምሮብዎ ይሆን? ራሰ በራ የሆነ ሰው ሲመለከቱ ምን ይሰማዎት ይሆን? አንዳንዶቻችን መምለጥ የስነልቦና ተፅዕኖ አሳድሮብን ይሆናል፡፡ በተለይ ምዕራባዊያን መላጣ ወንዶች የሴቶችን ቀልብ የመግዛት ግርማቸው እንደሚገፈፍ ያምናሉ፡፡ በእርግጥ ይህ በግልፅ ምክንያቱ ባይታወቅም በኛም ሀገር ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዳሉ ከሴቶቻችን ሁኔታ መረዳት ይቻላል፡፡ ይም ሆነ ይህ መምለጥን አስቀድመን ማስቀረት እንችላለን? በቅርቡ ለሕትመት የበቃን አንድ ጥናት ባነበብኩ ወቅት ለፅሑፌ መነሻ እንዲሆን ሻትኩ፡፡ ጥናቱ እስከዛሬ ስለራሰ በራነት ያልተነገሩ እውነታዎችን ለማስነበብ በቅቷል፡፡ በመሰረቱ ራሰ በራነት በጥንት ዘመን መጥፋት ሲገባው በትንሽ የዘረመል ስሕተት ከትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ የበቃ ለአብዛኞቹ የራስ ምታት፤ ለዘመኑ ተመራማሪዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መሆን ችሏል፡፡ አለመታደል ሆኖ ነው እንጂ የራሰ በራነት የዘረመል ቀመር ድሮ የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ውስጥ ሲያልፍ ሊጠፋ ሲገባው በትንሽ አጋጣሚ ከዘር ዘር እየተባዛ አሁን ላይ ላለው በሚልዮን ለሚቆጠረው ወፈሰማይ ሕዝብ መለያ ምልክት ሆኖ ሊቀር ችሏል፡፡ ሰዎች ለምን ፀጉራቸው ይሳሳል በመጨረሻም እንዴት ሊመለጥ ይችላል ብለን ብንጠይቅ አያሌ ምክንያቶችን እንሰማለን፡፡ ነገር ግን የሰው ፀጉር በምንም ዓይነት መልኩ ቢወድም ተመልሶ መብቀል እስከቻለ ድረስ አብዛኞቹ ምክንያቶች ተቀባይነትን ያጣሉ፡፡ አዲሱ ጥናት ምን ይላል? አብዛኞቹን ከዚህ ቀደም የነበሩ ጥናቶችን ይደግፋል፡፡ በዚህ መሠረትም አብዛኛው መላጣ ግለሰብ መምለጥ የሚጀምረው