Posts

Showing posts from April, 2017

የሳውና ባዝ ትዝብቶች ክፍል-3

ከዚህ ዘመናዊ ምድጃ ሥር በሚያፍን ሙቀት ውስጥ በላብ፣በውሃ፣በእንትን ታጥቤ እየተዝረበረብኩ ነው የተሰማኝን፣ ያየሁትን የማጫውታችሁ፡፡ከጊዜያዊው ስቱድዮ፡፡ለነገሩ እሳት ውስጥ ቋሚ ስቱድዮማ እንዴት ይታሰባል፡፡ መቼስ ያው በዓልም አይደል የኛ ቤት..(ይቅርታ የመንግስት ፍልውሃ) ግርግር ይበዛዋል፡፡ ለበዓል ንፅህናችንን ለመጠበቅ የምንፈፅመውን ተጋድሎ ሌላም ጊዜ ብንሞክረው ኑሮ…ዛሬ ግን ቶሎ መውጣት ፈልጌያለሁ፡፡ለምን ብትሉኝ ጓደኞቼ የሉም÷በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ደግሞ በፀጥታ ያካሉ፡፡ጥሎብኝ ጀርባውን የሚያክ ሰው ያሳቅቀኛል፡፡ ፊትለፊቴ ከተቀመጡት የሙቀት ምርኮኞች መካከል የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወጣት፤ የቆላ ዝንብ  የሚያህል (እንትን) ከጀርባው ላይ ዘግኖ በመገረም እያየው ሳለ እኛም ስላየነው ደንገጥ ብሎ፣ ‹‹እኛ ሰዎች እኮ ስንባል ቆሻሾች ነን…›› ከማለቱ ‹‹እሱ ፎከት እኮ ያንተ ነው እንጂ..›› አንድ በራ ጭንቅላት ሰው መልስ ከመስጠቱ፤በሳቅ ፀጥታችን ደፈረሰ፡፡ ከትንሽ ሰጣ ገባ በኋላ ድጋሚ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ እንዲህ ያልበላውን የሚያክ ከሚመስል ሰው ይህን ያህል ‹‹እንትን›› ከጀርባው ላይ ተቆፍሮ መውጣቱ ገርሞኛል፡፡ ማከኩ መታከኩ እንደቀጠለ ነው፡፡ የሰው ልጅ ጀርባውን እንዲያ ሲያክ እንዲህ ያለ ሲጥሲጥታ ይወጣል ብዬ አልገምትም ነበር፡፡ አጠገቤ የነበረን ጥቁር ልጅ ‹‹አባቱ መስታወትሽን እንዳትጎጂው›› አለው ከመጀመሪያው ጀምሮ በቅናት ዓይን ሲከታተለው የነበረ ጠይም አዳራ መሳይ ልጅ፡፡ ጥቁሩ ልጅ በንቀት ገላመጠውና ማከኩን ቀጠለ፡፡ ዛሬ አለም አቀፍ ጀርባ የማከክ እና ማሳከክ፣ መተካከክ፣እከክ…ቀን መስሎኝ ‹‹ቀኑ ዛሬ ምንድን ነው?›› ብዬ ልጠይቅ ዳዳኝ ወዲያው ተውኩት፡፡ ከሳውና ባዝ ተወልውለህ ስትወጣ ሰዎች ሁሉ ቆሻሻ እንደሆንን የምትረዳው በአፍንጫህ ነ