ቡና..ቡና
ልጅነትን ከሚያጣፍጡት እውነታዎች አንዱ ለነገሮች የምንሰጠው ልጅነታዊ እይታ ነው፡፡ መብላት፣ መጠጣት ፣መጫወት እንደምንም ብሎ ትምህርት ቤት አለመሄድ፤ በተለይ ነገ ትምህርት የለንም ወንዳታ! አቤት ደስ ሲል ፡፡ ልጅነት ደስ የሚል ጅልነትም ነው፡፡ ስለ ሒይወት የምንሰጠው ትርጉም፣ስለስነፍጥረት በራሳችን እውነት ነው ብለን የምንይዘው አቋም ወዘተ ልጅነትን እንድናፍቅ ያደርገኛል፡፡ ከልጅነት አሳዛኙና ቁጭትን የሚጭረው ነገር ቢኖር ልጆች እንደ ልጅ ተጫውተው፣ተጣልተው፣ተፋቅረው፣ሁሉን ነገር ሆነው ማደግ ያልቻሉ የያኔ አበባዎች የዛሬ ጎልማሶችና ወጣቶች ወይም አዛውንቶች ሕይወት ብቻ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ስለ እነዚህ አይነት ልጆች ወደፊት የሚለው ነገር ብዙ ቢኖረኝም ለዛሬ ግን አንድ ጥሩ ትውስታ ልጫርባችሁ፡፡ ይህ ትውስታ የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችሁ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ድሮ ድሮ ነው፡፡ ጧት ጧት፡፡ በተለይ ሰኞ ሰኞ ፡፡ ወደ ትምህርት ቤት መሔድ ከሚጠሉት ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበርኩ፡፡ በተለይ ሀይስኩል ላይ ትልቁ ፈተናዬ ከአልጋዬ ላይ መውረድ ነው፡፡ እኔ ከአልጋዬ ላይ ከምወርድ ሀገር በአፍጢሟ ብትደፋ ይቀላል፡፡ ሁል ጊዜ ጧት ጧት ውዷ እናቴ ጋር ከባድ ጦርነት እንገጥማለን፡፡ ፋዘር በዚህ ሰጣ ገባ ውስጥ ጣልቃ ለለመግባት ይጥራል፡፡ እርሷ ዝም ባትለውም ገለልተኛ አካል ለመሆን ይጥራል፡፡ ጧት በተለይ ሰኞ ጧት ይህ የተለመደ የማዘርና የኔ ጦርነት ዛሬ ላይ ፈገግ ከሚያደርጉኝ ትዝታዎቼ ውስጥ ትልቁ ነው፡፡ የሁለት ሰዓት ዜና ተነቦ ሲጠናቀቅ ይህ የተለመደና አንዳች ሃይል ያለውን ዜማ ስሰማ ስቅቅ ይለኛል፤ ብቻ በእንቅልፍ ልቤ ሆኜ አዳምጠዋለሁ፡፡ ‹‹የኢኮኖሚ ዋንጫ ቡና ቡና. ……………………. አውዳ ነው ቡናችን ቡና ቡና›› ግጥሙን በደን