...የፈረንጅ ግንባር!...
የዕለት ተዕለት ውሏችንን የሚያፋልስ፣ዕቅዳችንን የሚያናጋ፣ጊዜያችንን የሚጣብብ ነገር ቢኖር ወረፋ፣የቢሮ መስተንግዶ ምናምን ነው … ምክንያት ብላችሁ ስትጠይቁም … የመልካም አስተዳር ችግር፣የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምናምን ይሏችኋል … እናም በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት አንድ ጉዳይ ለማስፈጠም ሰሞኑን ስመላስ ከረምኩላችሁ፤ምንም መፍትሔ ላላመጣ፡፡ ምክንያቶቹን ብደረድርላችሁ አሰልቺ ይሆናሉና ልለፈው … እናላችሁ በዚህ ጭንቀት ውስጥ አንድ መፍትሔ ብልጭ አለልኝ ‹‹ ለምን የፈረንጅ ግንባር አልጠቀምም ›› አልኩ ለራሴ፤ ጉዳዩን ለ ‹ ፈረንጅ › ማለትም ለአለቃዬ አስረዳሁና ወደዛው የመንግስት መስሪያ ቤት ይዣት አመራሁ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ብዙ ቀን ደጅ ያስጠናኝ ግለሰብ በፈገግታ አለቃዬን ተቀበላት፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ አይቻልም ያለው ጉዳይ አሁን ያልቃል ሲል በተሰባበረ እንግሊዘኛ ዘፈነላት፤ ወይኔ ሀበሽ !... ቁጭቴ ስላበረደልኝ እስኪበርድልኝ ውጭ ወጣሁ … አለቃዬም ጉዳዩን ፈፅማ ተመለስን በፈጠርኩ ዘዴ ብደነቅም በሁኔታው ደግሞ ንዴቴ አንግብግቦኛል፤ ለምን እንደሆነ ከራሳችን ይልቅ ለፈረንጅ መስገድን እንመርጣለን፣እነሱም ይህን ስለሚየውቁ በሚገል የውሸት ፈገግታ እቃ እቃ ይጫወቱብናል !............... ዘይገርም ነገረ ሀበሽ እንግሊዝኛ ማወቅ የቋንቋ ሳይሆን የእውቀት መለኪያ የሆነበት ባለስልጣኖቻችን ሁሉ ብቃታቸውን ለመፈተሽ በተሰባበረ እንግሊዝኛ ሳይቀር በዓለም ሕዝብ ፊት የሚዋረዱበት፣በየትምህርት ቤቱ ሁሉ አማርኛ ማውራት