ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?
|
በ2014 40 በመቶ አውሮፓውያን ብቻቸውን ይኖራሉ፣
|
በ2018 በዓለም ላይ ዕድሜያቸው 30 የገቡ ግለሰቦች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት የቤተሰብ ጥገኛ ይሆናሉ
|
በ2019 ማሕበራዊ ድረገፆች ሁሉንም የዓለም ወጣት ላይ ተፅኗቸው ያርፋል፣
|
በ2026 በዓለም ላይ የግለኝነት ሕይወትን የሚመርጡ ወጣቶች ቁጥር ብቻ 20 በመቶ ይደርሳል፣
|
በ2038 ላጤዎች በአማካኝ በአንድ አገር ውስጥ ከፍተኛውን የጤና
እና የአእምሮ ቀውስ ተጠቂነት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡
|
ዱክ
ዩኒቨርሲቲ-2012(እ.ኤ.አ)
እንደ
መግቢያ ያስቀመጥኩት ጥናታዊ መላምት በቅርብ ጊዜ የተሰራ የምዕራባውያን ትንበያ ነው፡፡ እንደ መነሻነት ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለመመልከት ይጠቅማል ያሉ ተመራማሪዎች የዓለም
ሕዝብ አይኑን እንዲገልጥ ሲሉ ይፋ ያደረጉት ጥናትም ነው፡፡ የወንደ ላጤና የሴተ ላጤው ቁጥር በዓለም ላይ መጨመሩ ያሳሰባቸው የዱክ
ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስጋታቸውን ያሳዩበትም ሰንጠረዥ ነው፡፡ እያንዳንዱ ጋብቻ ወደፍቺ የማምራት ዕድሉ ከጊዜ አንጻር እየጨመረ በመምጣቱም
በብቸኝነት በሽታ የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥርን እንደሚጨምረውም ያስረዳሉ፡፡
እስኪ
ዛሬ በጥያቄ ልጀምር፡፡ ጥያቄዬን ለራሳችሁ ምላሽ ሰጥታችሁ ተከተሉኝም፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያችን ምን ያህሎቻችን በትዳር፣አልያም ከወላጆቻችን
ጋር፣ወይም በተቃራኒው ብቻችንን እየኖርን ነው ብላችሁ ትገምታላችሁ? ምን ያህል ብቻችንን ውለን ብቻችንን ማደርን እንችላለንስ?
ብቸኝነታችን ምን አሳጥቶታናል፣ምንስ እንድናገኝ ረድቶናል? እነዚህን ጥያቄዎች እንደ ግለሰብ መጀመሪያ መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ
ወንደላጤ አልያም ሴተ ላጤ ከሆኑ በመቀጠልም ሳይንስ የመረመረውን ሁኔታ ከራስዎ ጋር እያገናዘቡ ስለራስዎ አሳዛኙን ድብቅ ሕመም
እንመርምረው፡፡
አሜሪካዊቷ
የሳይንስ ፀሐፍት አብጌይል ቫን ቡረን ‹‹ብቸኝነት የመጨረሻው ትልቁ ድህነት ነው›› ትላለች፡፡ 21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ ሰዎች፤በተለይም
የድሃ አገራት ዜጎችንም ጨምሮ ግለኝነት፣ብቸኝነትና ከራስ ጋር የሚደረግ ኑሮ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንደመጣ፣የማሕበራዊ ሕይወት
መቀነስና የቴኖሎጂ ውጤተት የሆኑ ማህበራዊ ድረገጾች ተፅዕኖ በአብዛኛው የዓለም ዜጋ ላይ አሉታዊ እየሆነ መምጣቱ ማለትም ከአካላዊ
ግንኙነት ይልቅ ምናባዊ የሆነው የበይነ መረብ ግንኙነት እየጠነከረና እየበረታ መምጣቱ ዋነኛው ማሳያ ነው፡፡
በራሳችን
የእውቀት ደረጃም ብቸኝነት ምን አይነት ጉዳትና ጥቅም አለው ብለን እንጠይቅ፡፡በኛዋ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ጥናት ባይደረግበትም ከፍተኛ
ቁጥር ያለው ወጣት ሃይል በከተሞች ውስጥ የብቸኝነትን ኑሮ ይገፋል፤ከፍተኛ ቁጥር ያለውም መካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ሠራተኛ
ሐይልም አሁንም ድረስ ከቤተሰብ ጋር ይኖራል ብለን መገመት የምንችልባቸው ብዙ ማሳያ ምሳሌዎች እንደሚኖሩ እርግጥ ነው፡፡ ነገር
ግን ይህ ጥናት የሚፈልግ እንጂ በቀላሉ የምንደመድመው ጉዳይ አይደለም፡፡
አስፈሪው እውነታ
የትኛውም
የሳይንስ ዘርፍ በብቸኝነት ዙሪያ ጥሩ እይታ የለውም፡፡ እንደውም አስፈሪ የሆነ ድምዳሜ ላይ የደረሱ ብዙ የሳይንስ ዘርፎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም ኒውሮ ሳይንስ አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ
ሕክምና ሳይንስ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህልም በዱክ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው የቅርብ ወዳጅ የሌላቸው ወንደ ላጤና ሴተ
ላጤዎች 300 ፐርሰንት ያህል በልብ ሕመም የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው ይላል፡፡ ይህ በተቃራኒው ካገቡትና ከወለዱት እጅግ የራቀ
የልብ የመሥራት አቅም ስለሚኖራቸው ነው በማለት ምክንያታዊ ለመሆን ይሞክራል፡፡
የዬል
ዩኒቨርሲቲ ጥናት ደግሞ በትዳር ውስጥ ደስተኛ ሆነው የሚኖሩ ግለሰቦች ከወንደላጤና ሴተ ላጤ ግለሰቦች የተሻለና ያልተጎዳ የመተንፈሻ
አካለት ሥርዓት ይኖራቸዋል፤ዋነኛው ምክንያትም ከጭንቀትና መሰል የስነአእምሮ ፈተናዎች ተፅዕኖ የራቁ ስለሚሆኑ ነው፡፡ምክንያቱም ብቸኝነት ለጭንቀትና
መሰል የስነአእምሮ መንስኤ መሆን ስለሚችል ነው፡፡ እንደዚህ ጥናት አገላለፅ ከሆነ ደግሞ ወደ ሕመም የሚያመሩን ስሜቶች መካከል
ብቸኝነትና፣ጭንቀት አልያም ሀሳብ መብዛት ወደ ምግብ፣መጠጠና አደንዛዥ ዕፆች እንድናዘነብል ያደርጉናል በውጤቱም ወዳልተጠበቁ ሕመሞችና
ያልዕድሜ ለሚመጡ ሞቶች የመጋለጥ ዕድሉ ሰፊ ይሆናል፡፡
ሌላኛው
የአእምሮ ሳይንስ የሆነው ኒውሮ ሳይንስ ስለብቸኝነት አንድ ስሌት አለው፡፡ ግለኝነትን የሚመርጡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የራስ ወዳድነት
ስሜታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይመጣል፡፡ነገር ግን ከሌሎች ጋር በመቀራረብ የሚመነጩ ሆሮሞኖች እጥረት ይከስተባቸዋል፡፡ ለምሳሌ
ያህል ከሰዎች ጋር ስንቀራረብ፣ ማህበራዊ ሕይወት ላይ ሚና ሲኖረንና ጓደኞች ስናፈራና ስንቀራረብ በአንጎላችን ውስጥ የሚመነጩ ለሕይወታችን
ወሳኝ የሆኑ ኬሚካሎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ኬሚካሎች መካከል ዋነኞቹ ዶፋሚንና ሶሮቶኒን ናቸው፡፡
ዶፋሚንና
ሶሮቶኒን በፍቅር ግንኙነትና መሰል ቅርርብ ውስጥ የሚመነጩ ኬሚካሎች ሲሆኑ በአካላችን ላይ እጅግ ሃያል የሚባል ተፅዕኖ መፍጠር
ይችላሉ፡፡እስካሁን ድረስ ምርምሮች እንደደረሱበት ከሆነ እነዚህ ኬሚካላዊ ዑደቶች በሽታ የመከላከል አቅማችንን ይገነባሉ፡፡ በብቸኝነት
ለረጅም ዘመናት የሚኖሩ ሰዎችም በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ነው፤ይህንን አቅማቸውን የሚፈትኑ ቀለል ያሉ እንደ ጉንፋን ያሉ
የመተንፈሻ አካላታችንን የሚፈትኑ ሕመሞች ይጠነቅሩባቸዋል ይላል፡፡
ታድያ
ይህን ያህል አደገኛ ውጤት ያለው ችግርን እንዴት ልንመርጠው ቻልን? አያሌ ምክንያቶች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ 21ኛው ክፍለዘመን የካፒታሊስት
ስርዓት ውጤት የሆኑ የአኗኗርና የአመለካከት ዘይቤዎች ለዚህ ዋነኛ ምክንያት ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በተጨማሪም የቴክኖሎጂ ተፅዕኖው
ሌላኛው ዋና ምክንያት ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ግለኝነትና ስንፍናን እያሰፈነ እንደሆነ ብዙዎች ይከራከራሉ፡፡ እንደ አንድ ምክንያትም
ማሕራዊ ድረገፅ፣ስማርት ስልኮች፣ቪዲዮ ኮንፈረንሶች፣ሮቦቶች ወዘተ አካላዊ መስተጋብሮቻችን እንዲቀንሱ ምክንያት ሆነዋል፡፡
የወደፊቱ የዓለም ገፅታ
21ኛው
ክፍለዘመን አጋማሽ እስኪሆን ድረስ ማለትም 2050 ላይ እስክንደርስ ድረስ ፕላኔታችን በብዙ ነገሮች እንደምትታመስ እሙን ነው፡፡
ጦርነት፣ርሃብ፣የዓየር ንብረት ለውጥና ድርቅ፣ወረርሽኝ፣የሕዝብ ቁጥር መጨመር ሲሆን ከዚህም ባሻገር ቴክኖሎጂ አመጣሽ የሆነ አዲስ
የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን ብቸኝነት፣ግለኝነት የመሳሰሉ ችግሮችን የሚፈጥር ይሆናል፡፡ እኛ አፍሪካውያን በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ
አገራት በቀጣዮቹ ዘመናት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የሚጨምርባቸው አገራት ተብለው ተፈርጀዋል፡፡ ሆኖም ግን ማሕበራዊ ቀውስ ዋነኛ ተጠቂዎችም
ናቸው፡፡ በቤተሰብና በቤተሰብ ዙሪያ የሚኖሩ የማህበራዊ ቀውስ ተጠቂዎች
አገራት ተርታ ውስጥ ይቀመጣሉም፣ከዚህም ባሸገር ዜጎቻቸው ዘመናዊውን ሕይወት እየተቀበሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕይወቱን
በብቸኝነት የሚመራ፣ከማህበራዊ ኑሮ የተገለለ ትውልድ በሂደት እንደሚፈጠርም ይገመታል፡፡ አደጋውም እዚህ ላይ ያርፋል፡፡
በዚህ
ችግር ረገድ ምዕራባውያን ከወዲሁ ተጠቂ መሆናቸው በግልፅ እየታየ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል 2ሚልዮን እንግሊዛውያን በብቸኝነት ሕይወታቸውን
ይገፋሉ፤ ይህ ቁጥር በ2038 ዓ.ም በአንድ እጥፍ ይጨምራል፡፡ ፍቺዎች ከመቼውም በበለጠ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ ይመጣሉ፡፡ ይህ
ሂደትም በእያንዳንዱ ጋብቻ ላይ የፍቺ ዕድሉ ሰፊ እንደሚሆንም ይገመታል፡፡
በሌላ
በኩል ሰፊ የሚባል የቤተሰብ ሰንሰለት እየቀነሰ ይመጣል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ማህበራዊ ሕይወትን እየራቀ ይመጣል፡፡በተለይ
ከ50 እስከ 60ዎቹ ዕድሜ ያሉ ሽማግሌዎች ከፍተኛ የሆነ የልብ ሕመም አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡በተለይ ብቸኝነትንና የልብ ሕመምን
ምን እንዳያያዛው ሳይንስ አሁንም ግልፅ ባያደርግልንም በዚህ ችግር ከሚሞቱት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት እነዚህ ግላዊ ሕይወትን
የመረጡ ሰዎች እንደሆኑ ነው፡፡
ብቻቸውን
መኖር የመረጡ ሰዎች አሁንም ቢሆን ከባድ ውፍረትና የኮሌስትሮል ክምችት እንደሚኖራቸው የዴንማርካውያን ጥናት ያሳያል፡፡ ማህበራዊ
ሕይወት ለዚህ ጥሩ መፍትሔም ነው፡፡ ሰዎች ከሰዎች ጋር በሚኖረን ቅርበትና መስተጋብር በውስጣዊው አካላችን የሚካሄድ ጤናማ የሆነ
የሆርሞን ኡደት መኖሩን መዘንጋት የለብንም፡፡
በዚህ
በኩል ለጊዜው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አፍሪካውያን አገራት ስጋት አይኖራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን እስከ 2050 ድረስ ከፍተኛ ቁጥር
ያለው አምራች የአፍሪካ ዜጎች በስነልቦና፣ማህበራዊና ግለሰባዊ ቀውስ ውስጥ የሚፈትናቸውን የግለኝነት ኑሮ ከምዕራባውያን እንደሚወርሱና፤ተጠቂ
እንደሚሆኑ ጥናቶች ያስጠነቅቃሉ፡፡
ሌላው
ቢቀር ዛሬ ላይ የብቸኝነት ሕይወትን የመረጥን ግለሰቦች አንዳንድ ሕክምናዊ መፍትሔ ያላገኘንላቸው የስሜት ሕመሞች፤በተለይም አእምሯዊ
የሆኑት ድብርት፣መደበትና መሰል ችግሮች መፍትሔን መፈተሸ አለብን፡፡ ቢያንስ ተፈጥሯዊ ፍላጎታችንን ለማስተናገድ ፍቃደኛ መሆን አለብን፡፡
ሰዎችነን እና ከሰዎች ጋር እንኑር፡፡ ከሰዎች ጋር እንድንኖርም ተፈጥሮ ታስገድደናለችና፡፡
Comments
Post a Comment