ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?
በ2014 40 በመቶ አውሮፓውያን ብቻቸውን ይኖራሉ፣ በ2018 በዓለም ላይ ዕድሜያቸው 30 የገቡ ግለሰቦች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት የቤተሰብ ጥገኛ ይሆናሉ በ2019 ማሕበራዊ ድረገፆች ሁሉንም የዓለም ወጣት ላይ ተፅኗቸው ያርፋል፣ በ2026 በዓለም ላይ የግለኝነት ሕይወትን የሚመርጡ ወጣቶች ቁጥር ብቻ 20 በመቶ ይደርሳል፣ በ2038 ላጤዎች በአማካኝ በአንድ አገር ውስጥ ከፍተኛውን የጤና እና የአእምሮ ቀውስ ተጠቂነት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ዱክ ዩኒቨርሲቲ-2012(እ.ኤ.አ) እንደ መግቢያ ያስቀመጥኩት ጥናታዊ መላምት በቅርብ ጊዜ የተሰራ የምዕራባውያን ትንበያ ነው፡፡ እንደ መነሻነት ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለመመልከት ይጠቅማል ያሉ ተመራማሪዎች የዓለም ሕዝብ አይኑን እንዲገልጥ ሲሉ ይፋ ያደረጉት ጥናትም ነው፡፡ የወንደ ላጤና የሴተ ላጤው ቁጥር በዓለም ላይ መጨመሩ ያሳሰባቸው የዱክ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስጋታቸውን ያሳዩበትም ሰንጠረዥ ነው፡፡ እያንዳንዱ ጋብቻ ወደፍቺ የማምራት ዕድሉ ከጊዜ አንጻር እየጨመረ በመምጣቱም በብቸኝነት በሽታ የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥርን እንደሚጨምረውም ያስረዳሉ፡፡ እስኪ ዛሬ በጥያቄ ልጀምር፡፡ ጥያቄዬን ለራሳችሁ ምላሽ ሰጥታችሁ ተከተሉኝም፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያችን ምን ያህሎቻችን በትዳር፣አልያም ከወላጆቻችን ጋር፣ወይም በተቃራኒው ብቻችንን እየኖርን ነው ብላችሁ ትገምታላችሁ? ምን ያህል ብቻችንን ውለን ብቻችንን ማደርን እንችላለንስ? ብቸኝነታችን ምን አሳጥቶታናል፣ምንስ እንድናገኝ ረድቶናል? እነዚህን ጥያቄዎች እንደ ግለሰብ መጀመሪያ መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ ወንደላጤ አልያም ሴተ ላጤ ከሆኑ በመቀጠልም