Posts

Showing posts from September, 2014

….‹‹ክረምቱን በ‹ናዝሬት›…››……

ዘመን መፅሔት(ያልታተመ) እንደ ኑሮ ውሽንፍር የሚጋረፈውን የአቃቂ ብርድ የቀመስኩት ገና ከመኪና ከመውረዴ ነበር፡፡ ግን እኔ ብቻ ሳልሆን ያካባቢው ሰውም ውርጭ እንደጨመደደው ከፊቱ ስለሚታይ ተፅናናሁ፡፡ እኔና ባልደረቦቼ እንደምንም ብለን መናኸርያው ልንገባ ስንል የተለመደው የመናኸርያው ወጣቶች ወከባ ተቀበለን ።ለነገሩ ካዲስአባባ የምንሸሽ እንጂ ለስራ የምንሄድ አንመስልምም ‹‹ዝዋይ ናቹ አይደል!...ኑ!›› ጉተታው ተጀመረ ‹‹ልቀቃቸው ደብረዘይት ናቸው››   ሌላኛው ተናነቀው   ይሕኛው ደግሞ እሚጠነቁል ይመስላል።   ……‹‹ አቦ   ዞር በሉ ሞጆ ናቸው›› ሌላኛው ሁለቱንም ገፈተረ ወከባው   ያበሸቃት አንዲት ወጣት ደግሞ መልሷ ሁ ሉ አንድ የስራ ባደረባዬን አስታወሰችኝ ‹‹ ሻሸመኔ ነሽ›› ሲላት ‹‹አይ አሜሪካ ነኝ!›› በመልሷ ብሽቅ ያለው ወጣት ደግሞ ‹‹ በሕልምሽ እንኳን አትሔጅም!!!›› ሲላት እርሷም እኛም   ሳቅ በሳቅ ሆንን፣ በመሃል አንድ አቅሙን ያወቀ ቀጫጫ ወጣት   ያልታጠቡ አይኖቹን በጣቶቹ እየጨቆናቸው፣ ወደኔ ቀረበና ድምፁን ዝቅ አድርጎ   ‹‹ አዳማ ናችሁ አይደል?!›› ሲል ወደኃላ በሸሸው ጥርሱ ትክክለኛ አማርኛ ለማውራት ሞከረ፤ እንደኔ ግምት ግን አንዳንድ ቃላት በጥርሱ መሃከል ያመለጡት ስለመሰለኝ እንዲደግምልኝም ፈለግኩ   ደግሞ እኮ በዚህ ስራ ምን ያህል ዘመን እንደሰራ የሚያሳብቅበት ይመስላል፡፡ ብዙ ጊዜ ፀጉር ሲሸሽ እንጂ ጥርስ እንዲህ ወደ ኋላ ሲሸሽ ባለማየቴ ለመሳቅ ቃጣኝ…ግን በዝምታ መከተሉን መረጥኩ... በኌላም አንዱ መኪናው ውስጥ ወስዶ ዶለን፡፡ ገና ከመግባታችን ደግሞ ሹፌሩ በቅርቡ ታርጋው ተፈቶበት ነበርና የመንገድ ትራንስፖርት ሃላፊዋን በሌለችበት ከረዳቱ ጋ በመተባበር መሳደብ ጀምሯል፣