ያኔ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ሰሞን
መቼም እንደያኔው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የጦቢያ ባንዲራና የዋልያዎቹ መለዮ በቲሸርት፣በቁምጣ፣በቦዲ.. በፕላስቲክ አንባር ጠንከር ሲልም ግልጥ በሚታዩ ልባሶች፣ ጡት ማስያዥያ የሚመስሉ ነገሮች ሳይቀሩ ማለት ነው፡፡ ያኔ የተለመደውን ዙሪቴን ለማድረግ በአራት ኪሎ በኩል ወዳጆቼን ለማግኘት ዘልቄ ነበር፡፡ ነገር ግን የወዳጄቼን መቆየት አስታክኬ አንድ ጥግ ላይ ቁጭ ብለው ‹‹እ!..አለ የሚቀባ..ቀለም፣ቀለም…›› የሚሉ ወጣቶች ልጆች ወሬያቸው ሳበኝና ጠጋ ከማለቴ፣ ‹‹ነይ ቀዮ ይህን ቀይ ፌስሽን ላሸብርቀው በናት ሀገራችን ቀለም!›› ሳቅ እንደያዘኝ ‹‹ አታሸብርቀው ..ግን ሰው እየጠበቅኩነው፤ሰትቀቡም ለማየት ነው›› አልኩት ‹‹አብሽር ዱቅ በይ›› አለኝ፡፡ ቀለሙ ከምን እንደሚሠራ፣ማን እንዳመጣው ባይገባቸውም ብቻ ለዛሬም ቢሆን ለነዚህ ወጣቶች ትልቅ ገቢ ነው፡፡ ከሌላ አቅጣጫ ፊቱን በቀለም አዥጎርጉሮ የሚመጣውን ጓደኛቸውን ሲያዩት ፣ተንጫጩ፣የተረብ ናዳውን አወረዱት፤ ‹‹አንተ አንገትህን ዝቅ አግርገው ነው እንዴ የነከሩህ›› አለው አንዱ ሌላኛው ‹‹ ኒያላ ነው የምትመስለው እንኳን ዋልያ ልትመስል›› አንዱ ተቀበለና ‹‹አንተ እኮ ባትቀባም ዋልያ ትመስላለህ›› ፤ሳቅ በሳቅ ሆንን፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ… ‹ ‹ለከፋና ሽቀላ›› እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም ለከፋና ሽቀላ አብረው የሚሄዱ የዘመኑ ትዕይንቶች ናቸው፡፡ ቀለም ከሚቀቡት ወጣቶች አንደኛው አፉ የማያርፍ ዓይነት ነው፡፡ አላፊ አግዳመውን ለቀለም ከመጋበዝ ባለፈ ተረብም ጣል ያደርጋል፡፡ አንዲት ኮረዳ ቢጤ ብቅ ስትል፤ ‹‹እናቱ ልቀባልሽ…ውይ ይቅርታ ልቀባሽ›› ተሳሳቁ፡፡ በግልምጫ አንስታው አለፈ