‹‹ኦቨር ወጣሁ!››




‹‹ኦቨር ወጣሁ…›› አለችው ፊቷ ላይ በሚነበብ ጀግንነት፡፡ ምን ለማለት እንደፈለገች ቢገባውም በእነዚህ  ሁለት ቀናት ውስጥ የጠፋችበትን ምክንያት ማስረዳት መጀመሯ እንደሆነ ገብቶታል፡፡
‹‹ባይዘዌይ ለሳምንት ያህል ስልኬ ዝግ ይሆናል›› ይሄኔ ነገር ገባው መሰለች ከት ከት ብሎ ሳቀ፡፡
ፍቅር በሳምንት ውስጥ ክንፍ ያደርጋል፤ ነገር ግን ፍቅር በሁለት ቀን ውስጥ ይፈርሳል ብሎ አስቦትም አያውቅም ነበር፡፡
ፍቅር ሲያልቅ የሚታዩ ምልክቶችን እያየባት እንደሆነ ቢገባውም ከጀርባ የሆነ ነገር ሳይኖር እንደዚህ እንዳልሆነ ሆዱ ያወቀ ይመስል
‹‹የተፈጠረ ችግር አለ?›› ጠየቃት
‹‹ ኸረ በፍፁም…›› ከራሷ ጋር እየታገለች ትናገራለች፡፡ ምክንያቶቿ ሁሉ እርስ በእርስ መምታታቱ ትልቅ መልስ ነውና ዝምታን መረጠ፡፡
ከዛች የኦቨር ምሽት በኋላ  የመጣችው ፍቅሩ የእርሱ እንዳልሆነች ሲታወቀው፤ የሣምንቱ የፍቅር እብደት ማስታወስ ቀለለው ለውስጡ ሰላም ሲል፡፡
‹‹እንደዚህ ማንንም ወድጄ አላውቅም››
‹‹ከእንግዲህ በኋላ ጊዜዬን ላንተ ብቻ እሰጣለሁ››…….. እነዚህን የፍቅር ዜማዎች በሰማበት አንደበት  እነ ‹ኦቨር ወጣሁ›… ‹ባጋጣሚ ስላልተመቸኝ ላይህ አልችልም› የመሰሉ ማባረሪያ አዘል መልሶችን ሲሰማ ህሊናው ሞገተው
ይህ አይነት የፍቅር ገጠመኞቹ ብዙ ቢሆኑም አሁን ግን ሁሉም የሰለቸው ይመስላል
‹ሳትቀደም ቅደም›
‹ራስህን አድን›
‹አሁንስ ከማን ጋር እንደሆነች አታውቅም ግን ያለምንም ጥርጥር…› ከራሱ ጋር የተጣላ ሲመስለው ወሰነ፡፡
‹እድሜዋ ሲሮጥ ያኔ እርሷም ራሷን ለማዳን ትሮጥ የለ› አንድ እውነት አወቀ
የሚያብሰለስለው የፍቅሩ ፍፃሜ ከአእምሮው እንደ ጉም ሲቦን ታክሲ ውስጥ ቁጭ እንዳለ ተገነዘበ
የተሾመ በየነ አዳራሹ ቤቴ የሚለው ዜማ አነቃው፡፡ ‹‹አሁን ይህን ዜማ ማን በዚህ ሰዓት አመጣው? ሲፈልጉት ያልተገኘ…› በራሱ ተበሳጨ
ግጥሞቹ ደግሞ ውሥጡን ነካኩት
‹‹አዳሽ ገብቼ ከእልፍኝ እወጣለሁ፣
ለእመቤት ታምሜ ለገረድ እሞታለሁ››
‹ሆይ ጉድ አሁን ይህን ለምን እሰማለሁ፤ ከታክሴው አልወርደ ነገር› ሲል ከውስጡ ጋር እየታገለ ፣ እያቃረው ዜማውን በግድ ይሰማ ጀመር…
ተሾመ በየነ ማዜሙን  ቀጠለ
‹‹እንዲህ አይደለም ወይ ሰው ያለቦታው
ብሳና ይሆናል ሸንኮራ አገዳው
…………
‹ዝንጀሮ በገደል አድጦት አያውቅም
እንዲህ ያለ ዘመን አጋጥሞኝ አያውቅም
ከወዲያ የመጠች ያለላሙዳይ
የሴት ባልእንጀራ ውስጥ ውስጡን ገዳይ
በእንዲያ ያለዘመን ሲመሽ ተወልጄ
 ጅቡን ጋሼ እላለሁ ውሻውን ወድጄ
ያውና እዛ ማዶ በግ ያግዳል ሰው
ካላየ ካልሰማ ባላህያ ነው
……….
ይህን የመሰለ ዘፈን በቴዘመበት ዘመን ……..ወይ ዘመን ዛሬማ ፣ ፍቅር የለ፣ ዘፈን የለ ዘፋኝ የለ፡፡ እባብ ለባብ ይተያያል ካብ ለካብ የሆነ ዘመን፡፡
.......


‹‹እኔም ኦቨር ወጣሁ፡፡ የሂይወት ኦቨር፣ ሰው የመሆን ኦቨር ወጣሁ›› ደመደመ
 


Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?