Posts

የሳውና ባዝ ትዝብቶች-ክፍል 4

እነሆ የሰው ልጅ በሁለት እንደሚከፈል ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኩት ሳውና ባዝ ስገባ ነው፡፡ ልብስ ሲለብስና ልብሱን ሲያወልቅ፡፡ ዛሬ እዚህ እየታዘብኩት ያለው ሰው ልብሱን ያወለቀውን የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ ልብሱን፣ ዝናውን፣ዝናሩን ሲያወልቅ…ያው የሰው ልጅ ነው የሚመስለው፡፡ ያ ዓለምን የቀየረው፣ያ አራዊትን የገዛ፣ ያ ስልጣኔን የፈጠረ ፣ያ እራሱን ልዩ አድርጎ የሳለው የሰው ልጅ ልክ ልብሱን ሲያወልቅ ያው እንሰሳዊነቱ ይጎላል፡፡ ደሞ እኮ የሰውን ልጅ አካላዊ ቅርጽ ትክ ብዬ ሳየው ሌላኛው ግጣሙን ያላገኘ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ይመስላል፡፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ ራስ ጥፍሩ መግጠሚያውና መገጣጠሚያው ሌላ ቦታ የሆነ ሶኬት፣የሶኬት መቀበያ ወዘተ… አፉ ሶኬት፣ወንድነቱ ሶኬት፣ሴትነቱ ሶኬት፤ ብቻ የሰው ልጅ ወንድነቱን አውልቆ ሳ የው እሳታዊ ግጣሙ፤ኤሌክትሪካዊ አካሉ ከአንድ ቦታ ተነቅሎ ሌላኛውን ግጣሙን የሚፈልግ እቃ ይመስላል፡፡ ይቅርታ ይህን በራሴ ማየት ያልቻልኩት በኛ ሳውና ባዝ ክፍል ውስጥ መስታወት ባለመኖሩ ነው፡፡ ከፊት ለፊቴ መለመላውን የሚተራመሰው ሕዝበ አዳም ደግሞ ራሴን የማይበት በቂ መስታወት ነውና መስታወት ፍለጋ ምን ያደክመኛልስ? ዛሬ ከሳውና ባዝ ደምበኛና ወዳጄ ከድር ጋር ቁጭ ብዬ ነው ይህን የማውጠነጥነው፡፡ ሁለታችንም አቅም ስላነሰን ታችኛው ደረጃ ላይ ቁጭ ብለን ለብ ባለና ደረጃውን በጠበቀ ሙቀት እየተለበለብን ነው፡፡ ‹‹ዛሬ ደሞ ምንድን ነው ሁሉም ተፈራርቷል›› አለኝ ከድር፡፡ የሳውና ባዝ ጨዋታዎችን ልንቃርም እየጠበቅን፡፡ ‹‹ታገስ›› አልኩት ተዓምር የምጠብቅ እመስላለሁ፡፡ አጠገባችን የነበሩ ሁለት ጥርሰ ቡራቡሬ ሁለት ስክራፕ ሰጡን፡፡ ‹‹ይመቻቹ ያራዳ ልጆች›› አላቸው ከድር፤ አንደኛው የቡና ማልያ የመሰለ ጥርሱን ብልጭ አርጎ ‹‹ኸረ እኛ የመታ

የሳውና ባዝ ትዝብቶች ክፍል-3

ከዚህ ዘመናዊ ምድጃ ሥር በሚያፍን ሙቀት ውስጥ በላብ፣በውሃ፣በእንትን ታጥቤ እየተዝረበረብኩ ነው የተሰማኝን፣ ያየሁትን የማጫውታችሁ፡፡ከጊዜያዊው ስቱድዮ፡፡ለነገሩ እሳት ውስጥ ቋሚ ስቱድዮማ እንዴት ይታሰባል፡፡ መቼስ ያው በዓልም አይደል የኛ ቤት..(ይቅርታ የመንግስት ፍልውሃ) ግርግር ይበዛዋል፡፡ ለበዓል ንፅህናችንን ለመጠበቅ የምንፈፅመውን ተጋድሎ ሌላም ጊዜ ብንሞክረው ኑሮ…ዛሬ ግን ቶሎ መውጣት ፈልጌያለሁ፡፡ለምን ብትሉኝ ጓደኞቼ የሉም÷በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ደግሞ በፀጥታ ያካሉ፡፡ጥሎብኝ ጀርባውን የሚያክ ሰው ያሳቅቀኛል፡፡ ፊትለፊቴ ከተቀመጡት የሙቀት ምርኮኞች መካከል የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወጣት፤ የቆላ ዝንብ  የሚያህል (እንትን) ከጀርባው ላይ ዘግኖ በመገረም እያየው ሳለ እኛም ስላየነው ደንገጥ ብሎ፣ ‹‹እኛ ሰዎች እኮ ስንባል ቆሻሾች ነን…›› ከማለቱ ‹‹እሱ ፎከት እኮ ያንተ ነው እንጂ..›› አንድ በራ ጭንቅላት ሰው መልስ ከመስጠቱ፤በሳቅ ፀጥታችን ደፈረሰ፡፡ ከትንሽ ሰጣ ገባ በኋላ ድጋሚ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ እንዲህ ያልበላውን የሚያክ ከሚመስል ሰው ይህን ያህል ‹‹እንትን›› ከጀርባው ላይ ተቆፍሮ መውጣቱ ገርሞኛል፡፡ ማከኩ መታከኩ እንደቀጠለ ነው፡፡ የሰው ልጅ ጀርባውን እንዲያ ሲያክ እንዲህ ያለ ሲጥሲጥታ ይወጣል ብዬ አልገምትም ነበር፡፡ አጠገቤ የነበረን ጥቁር ልጅ ‹‹አባቱ መስታወትሽን እንዳትጎጂው›› አለው ከመጀመሪያው ጀምሮ በቅናት ዓይን ሲከታተለው የነበረ ጠይም አዳራ መሳይ ልጅ፡፡ ጥቁሩ ልጅ በንቀት ገላመጠውና ማከኩን ቀጠለ፡፡ ዛሬ አለም አቀፍ ጀርባ የማከክ እና ማሳከክ፣ መተካከክ፣እከክ…ቀን መስሎኝ ‹‹ቀኑ ዛሬ ምንድን ነው?›› ብዬ ልጠይቅ ዳዳኝ ወዲያው ተውኩት፡፡ ከሳውና ባዝ ተወልውለህ ስትወጣ ሰዎች ሁሉ ቆሻሻ እንደሆንን የምትረዳው በአፍንጫህ ነ

ቡሼ ክፍል 2

ዛሬ ደግሞ ቡሼ እትዬ ማርኮኝ በራፍ ባለች ድድ ማስጫ ድንጋይ ላይ ጭቁን ብሎ እንደተቀመጠ እያቀለሰ ነው፡፡ ሲንሰቀሰቅ ወደታች የሚታገለውን ንፍጡን ወደ ውስጥ እየሳበ፤ሲለውም በእጁ እየገፋ ሲያስነካው ንብረቱ ከእጁ እንዳይወጣ የሚታገል የዘመኑን ነጋዴ ይመስላል፡፡ የሚያለቅሰውም ለዚህ መስሎኝ ነበር፡፡ ምን ሞኝ ነኝ ስል አሰብኩ፡፡ ‹‹ምነው ቡሼ››  ጠጋ አልኩት፤ ቀና ብሎ እንኳን አላየኝም፤ፊቱን ወደአሊ ሱቅ አዙሮ የለቅሶውን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ በሚመስል ድምፅ በአዲስ ዜማ ያንበለብለው ቀጠል፡፡ ታናሽ ወንድሙ ጫጩ ከግቢያቸው እየሮጠ መጣ እና ጥያቄዬ እንደገባው ለማሳየት በሚመስል ፈገግታ ‹‹ልብሱ ላይ በእስኪብርቶ እየቸከቸከ...›› ሳያስጨርሰውና ለቅሶውን ሳያቋርጥ ቡሼ ያባርረው ጀመር፤ምስጢሩ እንዳይወጣበት ይመስላል፡፡ ትቻቸው ወደጉራንጉሩ ስዘልቅ የቡሼ ልብሶች ተሰጥተዋል፡፡ እነሱም በዝግታ ያልጠራ ውሃ ሲያንጠባጥቡ እንደቡሼ የሚያለቅሱ መሰለኝ፡፡ እነዚህ እንደበግ ቆዳ የለፉ ልብሶችን ዝቅ ብሎ ያላለፋቸው እግረኛ በግንባሩ ሳያብሳቸው አያልፍም፡፡ ዝቅ ያለ ዕድለ ቢስም ቢሆን ሳሙና የጠጣ የእብድ ምራቅ የሚያህል የውሃ ጠብታ ግንባሩን፣አልያም በራውን ሊያጠግቡት ይችላሉ፡፡ ትክ ብሎ ላያቸው የአንድን ሰው የተመሰቃቀለ የሕይወት ምዕራፎች ተሰቅለው እረፍት እያረጉ ይመስላሉ፡፡ ጠጋ ብዬ ሳስተውል ልብሶቹ ላይ እንደተባለውም የተሞነጫጨሩ ፁሑፎች ይታያሉ፡፡ ቆም ብዬ ስገረምማቸው ተደምረው ያላለቁ ቁጥሮች፣የማይገቡ ዓ/ነገሮች በተመሰቃቀለ አቅጣጫ ሰፍረዋል፡፡ እንደውም የተቦጨቀው ቲሸርቱ ላይ በተንጋደደ ፅሑፍ የተሳቀቁ ፊደሎች ‹‹ቃና ውስጤ ናዉ›› የተሳሳተ አጨራረስ በሚመስል ሰፍረዋል ‹ቡሼ ምን ነካው፤ከኛ ሰፈር ጩጬዎች ሁሉ ነቄው እሱ ነበር› ስል አሰብኩ

የኔ ትውልድ

‹‹አድናቂሽ ነኝ፤ መፅሔት ላይ አርፍሻለሁ›› አለኝ ያለምንም ሰላምታ፤የጅማ ቀረሮ ዛፍ የመሰለ ፀጉሩን በሁለት እጁ እያፍተለተለ፡፡ ወደፊት እንዳይከረበት ቢያሰጋኝም እሱ ወይ ፍንክች ጭራሽ ተጠጋኝ፡፡ ‹‹እ..እኔን ነው?›› ሳያስጨርሰኝ ‹‹አንዳንዴ ዘጭ የምታረጊው ፊዚክስ ጸዴ ነው!›› አብሮት የቆመው ልጅ ደግሞ አቋረጠውና ‹‹ፊዚክስ በአማርኛ ግን አይከብድሽም?›› ጠየቀኝ ‹‹እ…›› ገና ለማውራት አፌን ስከፍት ዕድል አልሰጡኝም፤ ‹‹ኸረ ላሽ እንዴት ያቅታል አንተ ደሞ…›› የመጀመሪያው ልጅ ቀጠለ፡፡ ፊዚክስ በአማርኛ እዛው አፍንጫዬ ስር  ክርክር ጀመሩ፡፡ አጠገባቸው መቆሜን የረሱኝም መሰለኝ፡፡ ሁለተኛው ልጅ ወደኩ አልወደኩ እያለ የሚያስፈራራውን ጅል ሱሪ በአንድ እጁ ከፍ እያደረገ… ‹‹እኔ እምልሽ አሁን ግን እዛ መፅሔት ላይ አላይሽም፤ ላሽ አልሻቸው እንዴ…ወይስ አቀዘቀዙሽ›› ፈገግ ለማለት ሲሞክር የተሰነጣጠቀ መስታወት አስታወሰኝ፡፡ ግራ እንደገባኝ ‹‹አይ…›› ተናግሬ ሳልጨርስ ሌላኛው ተቀበለና  ‹‹ኸረ እንኳንም ቀረብሽ ከዚህ በኋላ የራስሽን ደቅ አርገሽ ይሔን ፒፕል መገንተር ነው›› ‹‹ይኄን ፒፕልማ እንኳን ሳይንስ መድሃኔት ብትግተውም ገተታ ብቻ ነው!›› የመጀመሪያው ጨበሬ በቁጭት ያወራል፡፡ አሁን አስተውዬ ላያቸው ሞከርኩ፤የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይመስላሉ፡፡ እንዴ እንዴት ነው ነገሩ፤ እኔ ያልተሳተፍኩበት የራሴው ጉዳይ አፍንጫዬ ስር እየተወራ ምን ማድረግ አለብኝ፤ ምን እየተካሄደ ነው..ሆሆ.. ተገርሜ አልበቃኝም፡፡ ቀበቶውን የፈታ ሽማግሌ የመሰለ አሮጌ ታክሲ ሲመጣ  ተጋፍቼ፣ተገፍትሬ፣ተመትቼ፣ተረግጬ፣ተጨቁኜ ገባሁ፡፡ ‹‹ኸረ ላሽ ያንቺን እማ ዛሬ እኛ ነን ዘጭ የምናረግልሽሽ›› አለኝ ሱሪው ጅል ልጅ እንዴ አብረውኝ ገብተዋል እ

የባላንጣዎች ዕለት

ትኩረቴን የሚስብ እንግዳ ነገር ዓይኔን እረፍት ባይነሳው ኑሮ ማኪያቶዬን በተመስጦ መጠጣቴ ያለአንዳች ጣልቃገብ ሳይቋረጥ ይቀጥል ነበር፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው--ከፊት ለፊቴ ሁለት ጎልማሶች ወንድና ሴት ቁጭ ብለው እየተመገቡ ነው፡፡ ወንድዬዋ(ይቅርታ መጀመሪያ ሴት መስሎኝ ነበርና) ቶሎ ቶሎ ያወራል፤በእጁ አስሬ ይደባብሳታልም፡፡ሴትዬዋ ደግሞ ምንም የተለየ ስሜት አታሳየውም፡፡ በእያንዳንዱ ወሬዎቹ መጨረሻ ደሞ በቀኝ አይኑ ጥቅስ ያደርጋታል፡፡ (ነገሩን ገድየዋለሁ የሚል ይመስላል!) ‹‹እምልሽ….›› ይልና ሃሳቡን ሲጨርስ፤እየተወዛወዘ በቀኝ ዓይኑ ይዞ ጥቅስ ይሰጣታል፡፡ (አራት ነጥብ መሆኑ ነው!?) እንደገና በእንግሊዝኛ ይቀላቅልና፤አሁንም በቀኝ አይኑ ጥቅስ ያደርጋታል፡፡ (ፉልስቶፕ መሆኑ ነው ?!) እንዲህ ያለ ችሎታ ይገርማል፤አጠቃቀሱ፤የአጠቃቀስ ዲግሪ ያለው ይመስላል፡፡ እኔ እንደሱ ልሞክር ብል ከዚያ በኋላ ዓይኔ ወዴት አቅጣጫ እንደሚያይ ሳስብ ዘገነነኝ፡፡ … ድንገት ከደረት ኪሱ በቀይ ልብ የተሠራ አንድ ስጦታ ነገር አውጥቶ ሰጣት፡፡ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ልጅት በወንድ ኩራት ጀነን ብላ እያዳመጠች ነበር፡፡(መጀመሪያ ወንድዬዋ እሷ መስላኝ ነበር ) ስጦታው ሲመጣ ተነቃቃች፤ ፈታ ፈታ አለች፡፡አሁን ሴት መሆኗ አስታወቀ፡፡ ፈገግ ብላ ስጦታውን ስትቀበል፤ይሔኔ በፍጥነት በሁለት ዓይኑ ያዛትና በቀኝ ዓይኑ በጥቅሻ ደገማት፡፡ ፈገግ ብዬ ሰልጨርስ ድንገት ያለሁበትን ካፌ ቃኘት ሳደርግ ደነገጥኩ፡፡ አሁን ገና ገባኝ፡፡ ምናባቴ ነው እዚህ ጥልቅ ያደረገኝ፡፡ በቀይ አበባ፣በልብ ቅርፅ ያሸበረቀ፣ የተብለጨለጨ ካፌ ውስጥ ነኝ እንዴ፤ስገባ በራሴ አለም እየተወዛወዝኩ አላስተዋልኩም ነበር ማለት ነው፡፡ ተደናግጪ ለመውጣት ስጣደፍ፤ ከኋላዬ አንድ ሸካራ እጅ ጨመደደኝና ‹‹አ

የሳውና ባዝ ትዝብቶች ክፍል 2

ዛሬ ገና ተሸነፍኩላችሁ፤ዛሬ ገና ተረታሁ (በሌላ ነገር እንዳትተረጉሙብኝ)፡፡ የሳውና ባዝ ቆይታዬን አንዱ አሻሽሎ ፉት አላት፡፡ ለነገሩ ይህን ያህል ሳውና ባዝ ውስጥ የሚቆይ ሰው እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡ ሰውዬው ከሰመራ ነው የመጣሁት ሲልም የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ብቻ ‹‹ጥልቅ ሙቀት›› ውስጥ ቆይቶ ነው የመጣው (ያስታውቃላ)፡፡ቢሆንም ዶፒንግ ይመርመርልኝ፡፡  እኔ ግን እንደገባኝ ‹‹ጥልቅ እንትን›› ሳያስፈልገኝ አልቀርም፡፡ አስገራሚው ክስተት ደግሞ ከዚህ ይጀምራል-- እሳት በውሃ እየተቀቀልን ሳለ አንዱ ሰገጤ ተዝለፍልፎ ወረደ፤ ‹‹መሬት ያዝ! መሬት ያዝ!›› ሁለት ወፋፍራም ወጣቶች አዘዙት ‹‹ኸረ መሬት ለኛም አልበቃም›› ሌላ አንድ-አይና ወጣት መለሰ በግማሽ ፊቱ እየሳቀ ‹‹መሬት ላራሹ!›› አንዱ ከሌላኛው ጥግ ጮኸ ‹‹የ67 ዛር ያለቀቀው አሁንም አለ! ፤ ልቀቅ ‹በእንትን› ስም›› ከተቃራኒ አቅጣጫ ጮኸ ጫጫታው ቀጠለ፤ ስለ 67 አብዮት፤ ታህሳሱ ግርግር ሲወራ በመሐል የተዝለፈለፈው ሰገጤ ተረሳ! ሁኔታው ያናደደው ፤ግማሽ ጡት ሰውዬ፤ በላብ የተንጨፈጨፈ አንድ አይኑን ገሎ፤በሌላኛው እንዳፈጠጠ ‹‹ኸረ ልጁ ፌንት ነቀለ! ልጁ ሞተ እኮ›› ወሬው ቆመና ሁሉም ወደወደቀው ልጅ እያየ፤ጫጫታው ሳይቋረጥ ሁለት ዛኒጋባ ቅርፅ ያላቸው ልጆች አፋፍሰው አወጡት፡፡ በኋላ ላይ በእሳት ተቀቅለን እንደወጣን፤ሻወር መውሰጃው ላይ ሰዎች እየተጨቃጨቁ ደረስኩ፤ ሻወር ገብቶ አልወጣም ያለ፤ነፍሰጡር የመሰለ ወጣት ጋር ነበር ንትርኩ፡፡ ‹‹ባባ ለቅለቅ ብለሽ ልቀቂልን፤ጥልቅ ሻወር አልተባለም እኮ›› ‹‹አልወጣም!›› ‹‹ኸረ ፈጣጣ! ለምን?›› ‹‹እኛ ሰፈር ውሃ ከጠፋች…›› ሰይጨርሰው እየሳቅን ተውነው፤ ‹‹በፌስታል ይዘሽ ላጥ ነዋ፤መጨረሻ ላ

የቀዮች ጉዳይ

ዘወትር በሀበሻ ዜማ ውስጥ የምሰማው ለሀበሻ መልኮች፤ ውበት የተዘሜመ ስንኝ…በአማርኛ ብቻም ሳይሆን በሌሎቹ ቋንቋዎች…ጠይም..ጠይም አሳ መሳይ… ጠይም ናት ጠይም መልከ ሸጋ… ጥቁር ሰው… እንደጸሐይ የሚያበራው ጥቁር ውበቱ…ጠየም ያለ ሎጋ… ፒሪሪም ፒሪሪም.. ወዘተ…እኔ የምለው ግን ለቀይ ሰውስ? ቀይ ዳማ እንኳን ባቅሟ ተዚሞላታል…ለቀይ ሰው የተዜማ ነገር መፈለግ ዘበት ነው…ቢኖርም እንደው ለሞራላቸው/ችን እንጂ...ብቻ ቀይ ሰዎች የአገሪቱ ጠላት ዜጎች፤ወይም መጤዎች ይመስላሉ!   ግን አንድ ሁለት ትዝ የሚሉኝ ስንኞች… አንዱ ያላለቀ ስንኝ ነው ‹‹ቀይ የወደደና እባብ የነደፈው….›› ቤት መምቻው ተረስቶኛል…ያስታወሰው ይምታበት… ሌላ አንድ የሙሉ ቀን ዜማ አለች ደሞ…. ከወደዱም አይቀር ይወዳሉ ቀይ                                     እንዳላማ ሰንደቅ ከሩቅ የሚታይ ቤት መምቻው በግድ የተወረወረ ይመስላል፤ እንዲገጥምለት ብሎ ነው ልብል? ግጥሙ እንዲመታለት ብሎ እንጂ ቀይ ሰውን ለማድነቅ አይመስልም… እንደውም በዚህ ስንኝ ዝርው ውስጥ ከቀይ ሰው ይልቅ የሰንደቅ አላማው ድምቀት የጎላ ነው… ያሳዝናል፤አንድ እኛን የሚወክል ምርጥ ስንኝ ይጥፋ? አለ አንድ ቀይ ወዳጄ፤በቅጽል ስሞ ሶላቶ... ደሞ ጉድ እኮ ነው…ትንሽ ቀላ ያለ ሰው ስድቡ መከራ ነው…እኛ ጥልያንን ስለምናስታውሳቹ እንዲህ ጠመዳችሁን! አለ ይሄው ሶላቶው ወዳጄ…ቅናት ነው ልብል?! እስኪ ስንኝ አዋጡ ለቀያዮቹ አበሾች…? መፈክር እንዳታደርጉት ግን አደራ በቀዮ ይዣችኋለሁ!በዚህም ቀንታችሁ ነው እንዳትባሉ…