የሳውና ባዝ ትዝብቶች-ክፍል 4


እነሆ የሰው ልጅ በሁለት እንደሚከፈል ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኩት ሳውና ባዝ ስገባ ነው፡፡ ልብስ ሲለብስና ልብሱን ሲያወልቅ፡፡ ዛሬ እዚህ እየታዘብኩት ያለው ሰው ልብሱን ያወለቀውን የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ ልብሱን፣ ዝናውን፣ዝናሩን ሲያወልቅ…ያው የሰው ልጅ ነው የሚመስለው፡፡ ያ ዓለምን የቀየረው፣ያ አራዊትን የገዛ፣ ያ ስልጣኔን የፈጠረ ፣ያ እራሱን ልዩ አድርጎ የሳለው የሰው ልጅ ልክ ልብሱን ሲያወልቅ ያው እንሰሳዊነቱ ይጎላል፡፡ ደሞ እኮ የሰውን ልጅ አካላዊ ቅርጽ ትክ ብዬ ሳየው ሌላኛው ግጣሙን ያላገኘ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ይመስላል፡፡ ከራስ ጠጉሩ እስከ ራስ ጥፍሩ መግጠሚያውና መገጣጠሚያው ሌላ ቦታ የሆነ ሶኬት፣የሶኬት መቀበያ ወዘተ… አፉ ሶኬት፣ወንድነቱ ሶኬት፣ሴትነቱ ሶኬት፤ ብቻ የሰው ልጅ ወንድነቱን አውልቆ ሳየው እሳታዊ ግጣሙ፤ኤሌክትሪካዊ አካሉ ከአንድ ቦታ ተነቅሎ ሌላኛውን ግጣሙን የሚፈልግ እቃ ይመስላል፡፡ ይቅርታ ይህን በራሴ ማየት ያልቻልኩት በኛ ሳውና ባዝ ክፍል ውስጥ መስታወት ባለመኖሩ ነው፡፡ ከፊት ለፊቴ መለመላውን የሚተራመሰው ሕዝበ አዳም ደግሞ ራሴን የማይበት በቂ መስታወት ነውና መስታወት ፍለጋ ምን ያደክመኛልስ?
ዛሬ ከሳውና ባዝ ደምበኛና ወዳጄ ከድር ጋር ቁጭ ብዬ ነው ይህን የማውጠነጥነው፡፡ ሁለታችንም አቅም ስላነሰን ታችኛው ደረጃ ላይ ቁጭ ብለን ለብ ባለና ደረጃውን በጠበቀ ሙቀት እየተለበለብን ነው፡፡ ‹‹ዛሬ ደሞ ምንድን ነው ሁሉም ተፈራርቷል›› አለኝ ከድር፡፡ የሳውና ባዝ ጨዋታዎችን ልንቃርም እየጠበቅን፡፡ ‹‹ታገስ›› አልኩት ተዓምር የምጠብቅ እመስላለሁ፡፡ አጠገባችን የነበሩ ሁለት ጥርሰ ቡራቡሬ ሁለት ስክራፕ ሰጡን፡፡ ‹‹ይመቻቹ ያራዳ ልጆች›› አላቸው ከድር፤ አንደኛው የቡና ማልያ የመሰለ ጥርሱን ብልጭ አርጎ ‹‹ኸረ እኛ የመታሃራ ልጆች ነን›› አስፈገጉን፡፡ ‹‹ለናንተማ ይኼ በቲሸርት የመሄድ ያህል ቀላል ነው አደል›› አለ አንድ በጭለማ ውስጥ ስንፈልገው አልታይ ያለን ጥቁር ልጅ፡፡ ለመለቀድ መሞከሩ ነበር፡፡ ገላመጡት፡፡ ደንግጦ ዝም አለ፡፡ አይ ጥቁር ሰው፡፡
ከድር ሰልችቶታል፡፡ ጥሎኝ ወጣ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ተመለሰና ‹‹ና ዘሜ ጉድ አመለጠህ፤ድራማ እየተሠራ ነው፡፡›› አለኝ ፊቱ እየሳቀ፡፡ በፍጥነት ወጥቼ ወደመታጠቢያው ስመለከት፤ ሦስት ወጠምሻ ጎረምሶች ባላወቅኩት ቋንቋ እየጨቃጨቁ ወንድነታቸውን ያወዳድራሉ፡፡ የኔ ይበልጣል፣የኔ ይመዝናል፣የኔ አንበሳ… ይመስላል፤ከሁኔታቸው እንደተረዳሁት፡፡ ጉድ እኮ ነው! አንደኛው አጠር ቀጠን ያለው በትረ መኮንን የጨበጠ ያህል በአንድ እጁ ወንድነቱን እፍን አርጎ ይዞ በሌላኛው እጁ እየተወራጨ ይከራከራል፡፡ ትንፋሽ ያሳጠረው ነው የሚመስለው፡፡ እርግጥ በጥንታዊ ስልጣኔዎች ታሪክ የወንድነት መጠን የክብርና ታላቅነት ምሳሌ ነው እንጂ ሳውና ባዝ ውስጥ የሚያከራክር አልመሰለኝም ነበር፡፡ ሆ! ደሞ እኮ ትክ ብሎ ላየው የዶሮ አንገት የበጨጠ የዶሮ ነጋዴ ነው የሚመስለው፡፡ ሌላኛው ቦርጫም ቢሆንም ከሆዱ ስር የተደበቀች ጉዱን እያየ ያወራል፡፡ መደማመጥ ያለ አይመስልም፡፡ እኛንም አላፈሩም አልፈሩምም፡፡ ሦስተኛው ደግሞ እስኪ አገር ይመስክር በሚል ኩራት፤ወንድነቱን እየገላመጠ በጩኸት ያወራል፡፡ምን እያሉ እንደሆን መስማት ብችል ደስ ባለኝ፡፡ ግራ በመጋባቴም ለመሳቂያ ጊዜ አላገኘሁም፤ከድር ግን ፊቱን እስኪያመው ይስቃል፡፡ክርክሩ እንደቀጠለ በርቀት የሚታዘቡ ሽማግሌ በንቀት ራሳቸውን እየነቀነቁ ‹‹ኤድያ ይቺም እንትን ተብላ ነው፤የዘንድሮ ልጆች ደሞ ስንዝር ሁላ፤ወንዱ ስንዝር …›› ሌላ ጎባጣ ወጣት አቋረጣቸውና ‹‹ሴቱ ስንዝሮ›› አለ እየሳቀ፡፡ ድምፁ ከሴት የተቀዳ የሚመስል ጠይም ወንድ ደሞ ተቀበለና ‹‹ኸረ አባት የናንተ ዘመን ከዚህ ከበለጠማ ጃፓን ሰራሽ መሆን አለበት ማለት ነው›› አለ ሊያስቀን እየሞከረ፤ በንቀት ገላምጠውት እግራቸውን ሰበሰቡት፡፡ያየንባቸው መሰላቸው እንዴ! የእነዛ ጎረምሶች ክርክር ደሞ ቀጥሏል፡፡በጭቅጭቃቸው መሃል ወንድነቶቻቸውን ረስተዋቸዋል፡፡ የሦስቱም ወንድነቶች በክርክሩ መሃል የተጉላሉ ባለጉዳዮች ይመስላሉ፡፡ ወዲያ ወዲህ ያንገላቷቸዋል፡፡እርግጠኛ ነኝ የመጡበት አካባቢ መለመላቸውን መንጎራደድ ታላቅ የወንድነት ምልክት መሆን አለበት፡፡ የሆነው ሆኖ በማንኛውም አሸናፊነት እንደተስማሙ ባይገባንም እየተከራከሩ ቶሎ ተጣጥበው ቀና ብለው እንኳን ሳያዩን ወጡ፡፡ እኛም ጊዜያችን ሲደርስ ወጣን፡፡ ከድር ግን ነገሩ ውስጡ ቀርታለች መሰል ‹‹የረጅሙን ልጅ አይተኸዋል፤ አሎሎ ይመስላል…›› አሁን ሁኔታቸውን እያስታወሱ መሳቅ የበለጠ ያስቃል፤ያሳቅቃልም፡፡ ፍልውሃ ለዘላለም ትኑር!

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?

ግብረ ሰዶማዊነት፤ሌላኛው ጋሬጣ