የባላንጣዎች ዕለት


ትኩረቴን የሚስብ እንግዳ ነገር ዓይኔን እረፍት ባይነሳው ኑሮ ማኪያቶዬን በተመስጦ መጠጣቴ ያለአንዳች ጣልቃገብ ሳይቋረጥ ይቀጥል ነበር፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው--ከፊት ለፊቴ ሁለት ጎልማሶች ወንድና ሴት ቁጭ ብለው እየተመገቡ ነው፡፡ ወንድዬዋ(ይቅርታ መጀመሪያ ሴት መስሎኝ ነበርና) ቶሎ ቶሎ ያወራል፤በእጁ አስሬ ይደባብሳታልም፡፡ሴትዬዋ ደግሞ ምንም የተለየ ስሜት አታሳየውም፡፡ በእያንዳንዱ ወሬዎቹ መጨረሻ ደሞ በቀኝ አይኑ ጥቅስ ያደርጋታል፡፡ (ነገሩን ገድየዋለሁ የሚል ይመስላል!) ‹‹እምልሽ….›› ይልና ሃሳቡን ሲጨርስ፤እየተወዛወዘ በቀኝ ዓይኑ ይዞ ጥቅስ ይሰጣታል፡፡ (አራት ነጥብ መሆኑ ነው!?) እንደገና በእንግሊዝኛ ይቀላቅልና፤አሁንም በቀኝ አይኑ ጥቅስ ያደርጋታል፡፡ (ፉልስቶፕ መሆኑ ነው ?!) እንዲህ ያለ ችሎታ ይገርማል፤አጠቃቀሱ፤የአጠቃቀስ ዲግሪ ያለው ይመስላል፡፡ እኔ እንደሱ ልሞክር ብል ከዚያ በኋላ ዓይኔ ወዴት አቅጣጫ እንደሚያይ ሳስብ ዘገነነኝ፡፡ … ድንገት ከደረት ኪሱ በቀይ ልብ የተሠራ አንድ ስጦታ ነገር አውጥቶ ሰጣት፡፡ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ልጅት በወንድ ኩራት ጀነን ብላ እያዳመጠች ነበር፡፡(መጀመሪያ ወንድዬዋ እሷ መስላኝ ነበር ) ስጦታው ሲመጣ ተነቃቃች፤ ፈታ ፈታ አለች፡፡አሁን ሴት መሆኗ አስታወቀ፡፡

ፈገግ ብላ ስጦታውን ስትቀበል፤ይሔኔ በፍጥነት በሁለት ዓይኑ ያዛትና በቀኝ ዓይኑ በጥቅሻ ደገማት፡፡ ፈገግ ብዬ ሰልጨርስ ድንገት ያለሁበትን ካፌ ቃኘት ሳደርግ ደነገጥኩ፡፡ አሁን ገና ገባኝ፡፡ ምናባቴ ነው እዚህ ጥልቅ ያደረገኝ፡፡ በቀይ አበባ፣በልብ ቅርፅ ያሸበረቀ፣ የተብለጨለጨ ካፌ ውስጥ ነኝ እንዴ፤ስገባ በራሴ አለም እየተወዛወዝኩ አላስተዋልኩም ነበር ማለት ነው፡፡ ተደናግጪ ለመውጣት ስጣደፍ፤ ከኋላዬ አንድ ሸካራ እጅ ጨመደደኝና ‹‹አባቱ ሂሳብ!›› የሚል ድምጽ አዞረኝ፤አስተናጋጇ ነበርች፡፡ (ውይ ባለቤቱ መስሎኝ!)  ያለኝን የሌለኝን ሰጥቻት ጥርግ…ወይ አለማወቅ በባላንጣዎች ሜዳ ገብቼ ፋውል ሳልሰራ ተረፍኩ፡፡ እንኳንስ ጥቁሯን ማኪያቶዬን ጨረስኳት፡፡ (የኔ ባላንጣ እሷ ናትና!)

Comments

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?

ግብረ ሰዶማዊነት፤ሌላኛው ጋሬጣ