የቀዮች ጉዳይ



ዘወትር በሀበሻ ዜማ ውስጥ የምሰማው ለሀበሻ መልኮች፤ ውበት የተዘሜመ ስንኝ…በአማርኛ ብቻም ሳይሆን በሌሎቹ ቋንቋዎች…ጠይም..ጠይም አሳ መሳይ… ጠይም ናት ጠይም መልከ ሸጋ… ጥቁር ሰው… እንደጸሐይ የሚያበራው ጥቁር ውበቱ…ጠየም ያለ ሎጋ… ፒሪሪም ፒሪሪም.. ወዘተ…እኔ የምለው ግን ለቀይ ሰውስ? ቀይ ዳማ እንኳን ባቅሟ ተዚሞላታል…ለቀይ ሰው የተዜማ ነገር መፈለግ ዘበት ነው…ቢኖርም እንደው ለሞራላቸው/ችን እንጂ...ብቻ ቀይ ሰዎች የአገሪቱ ጠላት ዜጎች፤ወይም መጤዎች ይመስላሉ!
 ግን አንድ ሁለት ትዝ የሚሉኝ ስንኞች… አንዱ ያላለቀ ስንኝ ነው ‹‹ቀይ የወደደና እባብ የነደፈው….›› ቤት መምቻው ተረስቶኛል…ያስታወሰው ይምታበት…
ሌላ አንድ የሙሉ ቀን ዜማ አለች ደሞ…. ከወደዱም አይቀር ይወዳሉ ቀይ
                                   እንዳላማ ሰንደቅ ከሩቅ የሚታይ
ቤት መምቻው በግድ የተወረወረ ይመስላል፤ እንዲገጥምለት ብሎ ነው ልብል? ግጥሙ እንዲመታለት ብሎ እንጂ ቀይ ሰውን ለማድነቅ አይመስልም… እንደውም በዚህ ስንኝ ዝርው ውስጥ ከቀይ ሰው ይልቅ የሰንደቅ አላማው ድምቀት የጎላ ነው… ያሳዝናል፤አንድ እኛን የሚወክል ምርጥ ስንኝ ይጥፋ? አለ አንድ ቀይ ወዳጄ፤በቅጽል ስሞ ሶላቶ... ደሞ ጉድ እኮ ነው…ትንሽ ቀላ ያለ ሰው ስድቡ መከራ ነው…እኛ ጥልያንን ስለምናስታውሳቹ እንዲህ ጠመዳችሁን! አለ ይሄው ሶላቶው ወዳጄ…ቅናት ነው ልብል?! እስኪ ስንኝ አዋጡ ለቀያዮቹ አበሾች…? መፈክር እንዳታደርጉት ግን አደራ በቀዮ ይዣችኋለሁ!በዚህም ቀንታችሁ ነው እንዳትባሉ…

Comments

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?

ግብረ ሰዶማዊነት፤ሌላኛው ጋሬጣ