በጥዋት ቢሮዬ ኩርምት ያደረገኝ ብርድ ጋዜጣ ከማንበብ ግን አላገደኝም፡፡ እናም የዛሬውን አዲስ ዘመን እንደነገሩ አለፍ እያልኩ ስመለከት አንድ ዜና ትኩረቴን ሳበው... እንዲህም ይል ነበር
« የ10 በ90 የቤት ተመዝጋቢዎች በሙሉ በያዝነው የበጀት አመት ቤት ያገኛሉ» ይላል
«ከምራቸውን ነው እነዚህ ሰዎች?» ራሴን ጠየኩት
« እኔ እንጃ!?» ሌላኛም እራሴ መለሰልኝ
እናላችሁ ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳነብ 10 በ90 የተመዘገበው ህዝብ 23 ሺህ እንደማይበልጥና መንግስት ደግሞ24 ቤቶች
እንደገነባ ወይም ገብቶ ሊጨርስ እንደሆነ ያትታል፡፡ እውነት ይህ ከሆነ የሚቀጥለው አመት የሚንበሸበሸው ከተሜ
ታየኝ ግን ነገሩ ወዲህ ነው፡፡
10በ90 ሲነሳ ሁሌም አብሮ የሚነሳው የቤቱ ጥራት ነው፡፡ ያኔ ለምዝገባ ስንራወጥ ሁለት ጓደኛሞች ድንገት ተገናኝተው ሲጨዋወቱ ትኩረቴን ሳቡት
«10በ90 ነህ?» አንደኛው ጠየቀ
« አይደለሁም አለማየሁ ነኝ?» ሳቅ በሳቅ
«ባክህ አትቀልድ »
«አዎ ምንነው?» ለመስማት ጓጓ
« ቤቱ ምን እንደሚመስል አይተኸዋል ግን?»
« እሱንስ ተወው 10 ፐርሰንት ከፍሎ ቪላ የሚጠብቅ የለም፣ ግን የተመቸኝ ለ10በ90 የተሰጠው ስያሜ ነው»
«ማን አሉት ደግሞ?» ፈገግ ለማለት እየተዘጋጀ
«ወህኒ ቤት» ድጋሚ ሳቅ በሳቅ «አንዳንዶቹ ደግሞ ደሃ ማቆር» ይሉታል
ለምንድን ነው እንደዛ የተባለው?» በመገረም ጠየቀው በድጋሚ
« ዲዛይኑን ብታየው ቃሊቲን ያስታውስሃል፣ በቃ ቀጥ ብሎ መደዳውን በሮች ተደርድረውበታል»
ወሪያቸው ቢመቸኝም ጥያቸው ልሄድ ተገደደኩ
ከዚህ ቀደም እንደተባለውም 10 በ90 ከከተማ ወጣ ባሉ ቦታዎች የሚሰሩ ቤቶች ናቸው ይህ ደግሞ መሃል ከተማ
ከሚሰሩት 40 በ60 በጥራትም በተፈላጊነትም ልዩነት እንዳላቸው እናውቃለን፡፡ በሂደት ሁሉም ቤት ተሰርቶ ድሃው
ከከተማ ዳርቻ.፤ያለውና ጊዜ የሰጠው መሃል ከተማ መኖር ሲጀምር ብዙ ማህበራዊ ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ከነዚህ መካከልም
የፍቅር መስተጋብር አንዱ ነው ብለን እናስብና እስኪ በሃሳብ ወደፊት የሚፈጠሩ ወጣቶች እንዲህ አይነት ገጠመኞች
ይከሰቱባቸዋል ብለን እናስብ.....
እንበል እና አንድ 10 በ90 ቤት ውስጥ የሚኖር የድሃ ልጅ
ከተማ ብቅ ሲል ያያትን የ40 በ 60 ነዋሪ የሆነች ኮረዳ ለፍቅር ቢመኛትና ፍቅሩን መግለፅ የሚያዳግተው ሁኔታ
ቢፈጠር አዝማሪ ቤት እንዲህ ብሎ ሊቃኝ ይችላል፤
«ተቀበል!...ዲታዋን ወድጄ!...»
«ዲታዋን ወድጄ»... ተቀበለው....
ዲታዋን ወድጄ ፍቅሯ ማይረሳ
እኔ 10 በ90 እሷ 40 በ 60
አበቃሁ!
Comments
Post a Comment