ርዕስ አልባ ግጥም



ግጥም ከሃይለኛ ብዕረኛ የሚፈስ አንዳች ነገር ይመስለኛል፡፡ ፀሐፍት ሁሉ ገጣሚ መሆን አይችሉም፡፡ እርግጥ ገጣሚያንም ሁሉ ፀሐፍትን መሆን አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በሽነጣ ጣል የሚደረጉ ግጥሞች ነፍስ አላቸው፡፡ ለዛሬም ሲሸንጠኝ ጣል ያረግኋትን፤ዝናብ አልባ ሰማያትን ለመለማመን አንድ ያልኳት ግጥም ርዕስ አልባ ብትሆንም እንካችሁ ብያለሁ፡፡

.........

አያለቅስም አሉኝ ያገሬ ሰማይ፣
ያለዕንባ ዘለላ ይለቀሳል ወይ፣
ለካ እምባም ይገዳል ስማይም ሲከፋ፣
ወዲያ አላለቀሰ፤ወይ ዘለላው አልጠፋ፡፡
ቀረ ሲሉት አለ፣
መጣ ሲሉት ቀረ፣
ዕንባ እንዳቀረረ
(ማልቀስ ላቃተው የሰሜን ምስራቁን ሰማይ ለማባበል የተገጠመ)

Comments

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?