...የፈረንጅ ግንባር!...





የዕለት ተዕለት ውሏችንን የሚያፋልስ፣ዕቅዳችንን የሚያናጋ፣ጊዜያችንን የሚጣብብ ነገር ቢኖር ወረፋ፣የቢሮ መስተንግዶ ምናምን ነውምክንያት ብላችሁ ስትጠይቁምየመልካም አስተዳር ችግር፣የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምናምን ይሏችኋል
እናም በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት አንድ ጉዳይ ለማስፈጠም ሰሞኑን ስመላስ ከረምኩላችሁ፤ምንም መፍትሔ ላላመጣ፡፡ ምክንያቶቹን ብደረድርላችሁ አሰልቺ ይሆናሉና ልለፈውእናላችሁ በዚህ ጭንቀት ውስጥ አንድ መፍትሔ ብልጭ አለልኝ
‹‹
ለምን የፈረንጅ ግንባር አልጠቀምም›› አልኩ ለራሴ፤
ጉዳዩን ፈረንጅማለትም ለአለቃዬ አስረዳሁና ወደዛው የመንግስት መስሪያ ቤት ይዣት አመራሁ፡፡
እውነት እላችኋለሁ ብዙ ቀን ደጅ ያስጠናኝ ግለሰብ በፈገግታ አለቃዬን ተቀበላት፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ አይቻልም ያለው ጉዳይ አሁን ያልቃል ሲል በተሰባበረ እንግሊዘኛ ዘፈነላት፤ ወይኔ ሀበሽ!...ቁጭቴ ስላበረደልኝ እስኪበርድልኝ ውጭ ወጣሁአለቃዬም ጉዳዩን ፈፅማ ተመለስን
በፈጠርኩ ዘዴ ብደነቅም በሁኔታው ደግሞ ንዴቴ አንግብግቦኛል፤ ለምን እንደሆነ ከራሳችን ይልቅ ለፈረንጅ መስገድን እንመርጣለን፣እነሱም ይህን ስለሚየውቁ በሚገል የውሸት ፈገግታ እቃ እቃ ይጫወቱብናል!...............ዘይገርም ነገረ ሀበሽ
እንግሊዝኛ ማወቅ የቋንቋ ሳይሆን የእውቀት መለኪያ የሆነበት ባለስልጣኖቻችን ሁሉ ብቃታቸውን ለመፈተሽ በተሰባበረ እንግሊዝኛ ሳይቀር በዓለም ሕዝብ ፊት የሚዋረዱበት፣በየትምህርት ቤቱ ሁሉ አማርኛ ማውራት የሚያስቀጣበት ወዶ እጁን ለዘመናዊ ቅኝ ግዛት የሰጠ ሕዝብ መጨረሻውን ለማየት እጓጓለሁ፡፡ ሌላው ቢቀር ይህ ትውልድ ያኔ ጥልያን ስትዘምትብን ቢፈጠር ኑሮ የባርነት ሰንሰለቱን በፍቃደኝነት አንገቱ ላይ ያስር ነበር ብዬ እሰጋለሁ…

Comments

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?