ውበትን ፍለጋ

ዛሬ ቁጭ ብዬ የምዕራባውያንን ዜና እየኮመኮምኩ ነው፡፡ አንድም ቢሆን በሚመርጡት የዜና ታሪክ መልዕክቶቻቸው ላይ ከፊትለፊትም ይሁን ከጀርባ ትልቅ ፣ከባድ መልዕክት ያላቸውን ሳያጠኑ፣ሳይመዝኑ በፍፁም እንካችሁ አይሉም፡፡ ምዕራባያን የዜና አውታሮቻቸው ከመድፍና፣ከታንክ የበለጠ አለምን እንደሚደመስሱባቸው ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ሌላው ቢቀር በሕይወት ዘመኔ ካየኋቸው እጅግ ስሜትን ከሚፈትኑ ዘጋቢ ፊልሞች መካከል የቢቢሲ big stories 2014 በሚል የዘጋቢ ፊልሞች ተከታታይ ዝግጅት መካከል ሊሳ ዱሴት (በእድሜ ጠና ያለችው የእንግልጣ ጋዜጠኛ) የሰራችው (#children_of_Syria) አንዱና ብቸኛው ነው ብል ማጋነነን አይሆንብኝም፡፡ የዛን ያህል ደግሞ ለኛ አፍሪካውያን ያላቸው አመለካከት ያናድደኛል ብቻ ሳይሆን ባገኛቸው ራሱ የምለቃቸው አይመስለኝም…አያስቅም..እውነቴን ነው…ዛሬ ያየሁትም ዜና አዘጋጁንም ዘጋቢዋንም ባገኛቸው አርባ ምክር ሊለውጣቸው ስለማይችል አርባ ጅራፍ አዝላቸው ነበር፡፡
ወደ ገደለው እንመለስና የዜናው አውታር አልጀዚራ ነው፤ድንገት ከዜናዎቹ መካከል አንድ አስገራሚ በተለይም ምዕራባውያንም ሆኑ አረቦች በጥቆሮች ላይ ያላቸውን የዘረኝነት አቋም በተዘዋዋሪ የሚያሳይ (ባጭሩ ፈረንጆች በጥቁሮች ላይ ሙድ የሚይዙበት)ዜና ብቅ አለ፡፡ ዜናው ሆን ተብሎ እንደተመረጠ ከዜናው ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡
‹‹አርቴፊሻል ፀጉር በናይጄሪያውያን ሴቶች ዘንድ ተወዳጅና ገበያው የደራ እየሆነ መጥቷል ›› አለች በናይጄሪያ የአልጀዚራ ዘጋቢዋ ፈገግታ ከፊቷ ሳይጠፋ፡፡ ዞር ዞር ብላ ያነጋገራቸው ሴቶችም የሰጡትን አስተያየት ስሰማ እንደ አፍሪካዊነቴ አፍርሁ፡፡
አንድ ፀጉር ያጠራት ናይጄሪያዊት ወጣት ከህንድና ጃፓን የሚመጡ ጸጉሮችን ለምን እንደምታደርግ ስትናገር፣
‹‹የራስ መተማመኔ ይጨምራል፣ውበቴ ይጎላል፣ከሰው ፊት ስቆም ኩራት ይሰማኛል፣ሙሉ ሰው የሆንኩ ይሰማኛል›› ደረደረችው… ምንቅር ምንቅር እያለች፣ ‹‹እስኪ ምን ታመጡ!›› የምትል ትመስላለች፡፡
‹‹ምን…;???›› አልኩ ለራሴ እንደደነገጥኩ፤… የሰው ጠጉር መቀጠል ሆነ እንዴ የራስ  መተማመን?
 ይችን ‹‹ሙሉ ሰው የሆንኩ ይመስለኛል›› የምትለዋን  አባባል ደግሞ መዝግቡልኝ፤ታበሳጫለችም፡፡ ለካ ተፈጥሮ ሙሉ አድርጋ እንደላከቻቸው የማያምኑ ግኡዛንም አሉ፡፡
ወቸው ጉድ … የኛ ሴቶችስ ምን ይሰማቸው ይሆን? የፈረንጅ ጭራ ቁጭ ብለው ሲያስቀጥሉ?
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ደግሞ
‹‹አንድ ሰዓትም ይሁን ሁለት ሰዓትም ይፍጅ ቁጭ ብዬ መሰራቱን እመርጣለሁ››አለች፡፡ የዚች ጠጉር አልባ ናይጄሪያዊት አባባል ደግሞ የገብረ ክርስቶስ ደስታን ‹‹ጊዜ›› የምትለዋን ግጥም ትዝ ያሰኘኛል፡፡ ‹‹ጊዜ እንቅልፌን ከምተኛበት ከአፍሪካ ምድር ገባሁ›› የምትል መልዕክት ያላትን ግጥም ማለቴ ነው፡፡
በዜናው የመደምደሚያ አንቀጽ ላይ አያሌ ናይጄሪያውያን ሴቶች በከተማ ውስጥ የፈረንጅ፣የህንድ፣ የጃፓን ቁርጥራጭ ፀጉር በአናታቸው ላይ ቀጥለው ሰው ሰራሽ ዝንጀሮ እስኪመስሉ ድረስ እየታዩ በከተማቸው ላይ ውርውር ሲሉ በዜናው ቪድዮው ታየ፡፡
እኔ ግን ጥያቄዬ አላለቀም፡፡ ውበት ለሴቶች መገኛው ምኑ ጋር ነው? ለጥቁር ሴት ውበት ማለት የምዕራባያን ሥራ ውጤትን መገልገል ነው? ሴት ልጅ ለውበቷ ስትል የምትከፍለው መስዋትነት አንድ ሀገር ድሆቿን ለመታደግ ከምታደርገው ጥረት ለምን ይበልጣል ? በእርግጥ ፀጉር ለሴት ልጅ ውበት ነው ነገር ግን ተፈጥሮ ከሰጠችን የፀጉር ፀጋ ውጭ የሰው ጸጉር መቀጠል ሰው ሰራሽ እንጂ ተፈጥሮ ሰራሽ እንደማያስመስል ይሰማኛል፡፡ ለነገሩ ‹‹ሲያጌጡ ይመላለጡ›› ‹‹ሲጌጡ ያገጡ›› ምናምን ይባል የለ በአማርኛስ ቢሆን…በኛ ሴቶች አርቴፊሻል ጠጉር ፍቅር ስገረም ናይጄሪያውያን ሴቶች ደግሞ ግዴታ አስመስለውታል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ምዕራባውያን እንዲሳለቁብን ትልቅ እድል ፈጥሯል፡፡
ናይጄሪያ ውስጥ የአርቴፊሻል ጸጉር ማምረቻ እና የተፈጥሮ ጸጉር መሸጫ የከፈተ የኢስያ ሰው፣ለጋዜጠኛዋ፤በኢንዶኔዢያ የተሰባበረ እንግሊዝኛ ‹‹እድሜ ለአፍሪካውያን ሴቶች›› ይላል ረብጣ ብሩን እየቆጠረ፡፡ ዜናው በዚህ መንፈስ አልቆ ወደሌላ ዜና ርዕስ እስኪያልፍ ግርምት ጭርብኛል፤ደግሞ እኮ ምዕራባውያን ይህን ዜና ብለው ሲያሳዩ ነገር ፍለጋ እንጂ ለኛ አዝነው አለመሆኑ እየገባኝ ንዴቴም እንዳለ ነው፡፡
እስከመቼ በተፈጥሮ ተክለ ሰውነታችንና በጥቁርነታችን እንደተሸማቀቅን እንደምንቀጥል ባላውቅም አሁን ግን ሴቶቻችን ገና ብዙ ያሳዩናል፤ገና ብዙ ተሸማቀው ያሸማቁናል፡፡ ናይጄሪያዊ አለመሆኔ ከቁጭት ቢገላግለኝም የኛ ሴቶች የሚሆኑትን ስለማውቅ ደግሞ በራስ መተማመን ደረቴን ልነፋ አልቻልኩም፡፡አልችልምም፡፡ሴቶቻችን ይህን የፈረስ ጭራ የመሰለ የውሸት ጠጉር ወዲያ እስካልጣሉ ድረስ ሴቶቻችን እንደ ‹ሴት› ሊታዩኝ እንደማይችሉም ተሰምቶኛል ‹‹እስኪ ምን ታመጡ!›› የምል እመስላለሁ ይህን ስል!... ሎል

Comments

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?