መድሀኒትዎን በ3ዲ እቤትዎ ቁጭ ብለው የሚያዘጋጁበት መሳሪያ.....
ምትሀት
የሚመስለው የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ በሁሉም ምዕራባውያን ቤት ውስጥ ሊገባ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀረዋል፡፡
ኮምፒዩተሮች ድሮ ለፕሮግራም አዋቂዎችና
ባለሞያዎች ብቻ ነበሩ፤ዛሬ ግን በየሁሉም ቤት ውስጥ መግባት ችለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም አጅብ የሚያሰኙ ግኝቶች ተፈጥረዋል፡፡
አዲሱ ግኝት የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ ተብሎ ይጠራል፡፡ በቤትዎ ሆነውም መድሀኒትዎን እሚያትሙበት እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ ነው፡፡
ከእርስዎ የሚጠበቀው እቤትዎ የሚደርስ
ኢንተርኔት እና አዲሱን ከፈረንጆቹ ግንቦት ወር በኋላ ለገበያ የሚቀርበውን የ3ዲ ማተሚያ ማሽን መግዛት ብቻ ነው፡፡ ከዛም
የራስዎ ሀኪም ሆኑ ማለት ነው፡፡ እንዴት ይሆናል ብለውስ ጠየቁ? ነገሩ ወዲህ ነው፤ በእስኮትላንድ ግላስኮው ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ
በ ሊ ክሮኒን የሚመራ የኬሚስትሪ ምሁራን የምርምር ቡድን ለመድሀኒት መቀመሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎችን ቀመርና 2000 የአሜሪካን
ዶላር የሚፈጅ የ3ዲ ማተሚያ ማሽን በመጠቀም አስገራሚ የሆነ ግኝት ፈጥረዋል፡፡
የ3ዲው ማተሚያ በቀላሉ የቤተሙከራ
መድሀኒት መቀመሚያ እቃዎችን የሚተኩ ዘመናዊ እቃዎችን በውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡ በሚታዘዝበትም ወቅት አስፈላጊውን የመድሀኒቶቹን
ውህዶች ይቀምማል፤ በመጨረሻም የሚፈለገውን የኬሚካል ውህድ ፈጥሮ መድሀኒቱን ይሰራል ወይም በዘመነኛው የመሳሪያው አጠራርም
መድሀኒቱን ያትማል ማለቱ ይቀላል፡፡ “ኬሚስትሪን ለሁሉም
ሰው የማስተዋወቅ ያህል ይሆናል፤ኬሚስትሪ ያን ያህል ከባድ በማይሆንበት ሁኔታ ሰዎች የሳይንስ ፍሬዎችን እንዲጠቀሙ የማድረግ
ያህል ነው፡፡” ይላል የግኝቱ ባለቤት ሊ ክሮኒን፡፡ በተለይ ሕክምና በቀላሉ የማይደርስበት አካባቢ ሰዎች የራሳቸውን የራስ
ሕመም ክኒን ወይም ሌላ መድሀኒት በአፋጣኝ አዘጋጅተው ራሳቸውን ከድንገተኛ አደጋ እንዲታደጉ ሊረዳ እንደሚችልም ያምናል፡፡
መድሀኒትም
መታተም ይችላል?
ቃሉን በቀጥታ ከፈረንጅኛው ወስደን
“መታተም” ያልነው ምክንያት ስላለን ነው፡፡ ዋነኛው ምክንያት ማተሚያ መሳሪያው ያዘዝነውን የመድሀኒት አይነት ፎርሙላ ወይም
ቀመር በሕትመት አይነት ዘዴ ያትማል ይህ ሕትመትም በብሉ ሬይ ቴክኖሎጂ አማካኝነት በማተሚያው በሚገኘው የኬሚካል መቀመሚያ
ገንዳ መሰል እቃ ውስጥ መድሀኒቱን ያዘጋጃል፡፡ የሚዘጋጀውም ማሽኑ በተሰጠው ቀመር መመሪያ መሰረት ነው፡፡ ሕገወጥ የሆነ
መድሀኒትምርትንም ለማስቀረት ተመራማሪቹ ዘዴ ፈይደንለታል ይላሉ መፍትሔውም ይህን ማሽን የገዛ ማንም ሰው የሚተመውን መድሀኒት
ቀመር ዝርዝር መረጃ ሳይሆን ተሰርቶ ያለቀውን ቀመር ብቻ ከኢንተርኔት ዳውንሎድ በማድረግ ብቻ እንዲጠቀም ይደረጋል፡፡
ከኢንተርኔት
ዳውንሎድ የሚደረጉ መድሀኒቶች?
የምንፈልገውን
የመድሀኒት አይነት በ3ዲ መሳሪ በቤታችን ለማዘጋጀት ስንፈልግ የመድሀኒቶቹን አይነት በቀጥታ ከኢንተርኔት ዳውንሎድ ማድረግ
ይጠበቅብናል ነገርግን ዳውንሎድ የምናረገው የመድሀኒቱን ቀመር እና ዝርዝር ሁኔታ የያዘ ሶፍትዌር ነው፡፡ ሶፍትዌሩ በ3ዲ
ማተሚያ ውስጥ ሲጫን ማተሚያው በሶፍትዌሩ ትዕዛዝ ኬሚካሎችን በውስጡ በመቀመም ያዘጋጃል፡፡ ማሽኑ ኬሚካሎችን ለመቀመም
የሚያስችለው የኬሚስትሪ የተሟሉ ዕቃዎችንም አካቷል፡፡ በእርግጥ አነስተኛ እ የአንድ ፎቶ ኮፒ ማሽንን የሚያክል ይዘትና ስፋት
ቢኖረውም ልዩና ዘመናዊ የሆነ ስራዎቹን የሚቆጣጠሩበት ኮምፒዩተር ተገጥሞለታልም፡፡

መጀመሪያ
የመድሀኒት ወይም ኬሚካል ሶፍትዌር ወይመ ብሉፕሪንት ቀመር ዳውንሎድ እናረጋለን
|
በመጨረሻም
በፕርንቱ ውስጥ የኬሚካል ውሕድት ይፈፀማል ወጤቱም በትክክል የተዘጋጁ የመድሀኒቶች ውህድ ይፈጠራሉ፡፡
|
በመጨረሻም
በፕርንቱ ውስጥ የኬሚካል ውሕድት ይፈፀማል ወጤቱም በትክክል የተዘጋጁ የመድሀኒቶች ውህድ ይፈጠራሉ፡፡
|
የምሁራኖቹ ተስፋ
በሼፊልድ
ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ የናኖ ቴክኖሎጂ ባለሞያ ሪቻርድ ጆንስ “የኬሚትሪ ባለሞያዎች በታሪካቸው ከጥቂት አጋጣሚዎች ውጭ ስማቸውን
የሚያስጠራ ስራዎችን ከሰሩ ብዙ ጊዜያት አልፈዋል፡፡ ዘንድሮ ግን በጣም ተሳክቶላቸዋል፡፡” በማለት የግኝቱን ተስፋ ሰጪነት
ይጠቁማል፡፡ የኬሚስትሪ ትልቁ ፈተና ሆኖ የቆየውም መድሀኒቶችን በሕገ ወጥ የሚያዘጋጁ ሰዎች እጅ ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ
ብዙውን ጊዜ ፈተና የሆነ ጉዳይ ነው፡፡አዲሱ የ3ዲ መድሀኒት ማተሚያ መሳሪያ ግን በራሱና ለራሱ ብቻ አበጅቷል፡፡ ከኢንተርኔት
ዳውንሎድ የሚደረጉ የኬሚስትሪ ቀመሮችን የሚጠቀም ቢሆንም እነዚህ ቀመሮች በሀከሮች እንዳይዘረፉ ለማድረግ ተሰርተው ያለቁ
የመድሀኒቶችን ቀመሮች ብቻ ይቀበላል፡፡
ወደፊት ክሮኒንና የስራ ባልደረባዎቹ በዚህ ማሽን የሚታተሙ የቤተ ሙከራ
ውጤቶችን አይነት ለማብዛትና ለማሳደግ አቅደዋል፡፡ በአሁን ሰዓትም በሞባይልዎ ላይ በሚጫንልዎ ሶፍትዌር ወይም ከማተሚያው ጋር
በሚገጠም ኮምፒተርዎ ሆነው መድሀኒቱ ሲዘጋጅ ቁጭ ብለው የኬሚካሎቹን ውሕደት ምን እንደሚመስል መከታተል ይችላሉ፡፡ ሪቻርድ
ጆንስ ይህንን ሁኔታ ሲናገርም “እቤት ቁጭ ብሎ ምግብ የማብሰል ያህል ይመስላል፡፡” በማለት በማሽኑ ብቃትና ሁኔታ ያስደነቀውን
ይናገራል፡፡
ማሽኑ
በተወሰነ ደረጃ የሚቀሩት ነገሮች እንዳሉ ክሮኒን ያምናል፡፡ ክሮኒን እንደሚናገረውም የኬሚካል ሪአክሽን(ውሕደት) በሚከናወንበት
ወቅት የሚፈጠሩ የማተሚያው በውስጥ የሚለኮሱ እሳቶች ኦክስጅን ቢያገኛቸው ፍንዳታ የመፍጠር አቅም ስላላቸው ይህን ችግር
አስተካክለው በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ለዕይታና ለትልልቅ ተቋማት ለገበያ እንዲውል አቅደዋል፡፡ይህንንና ሌሎች ማስተካከያዎችን
በማድረግ ወደፊት በሰፊው ለሕዝብ ገበያ ለማዋል ሕልም አላቸው፡፡
በኖርዝዌስተርን
ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ባለሞያ የሆነው ፍሬዘር ስቶዳርት ግኝቱን አስመልክቶ “ሁላችንንም ያነቃቃ ስራ ነው” በማለት በኬሚስትሪ
ተመራማሪዎች መሀከል የፈጠረውን ስሜት ይጠቁማል፡፡ ከባድና ብዙ ሒደት የሚጠይቁ መድነሂቶችን ለማምረት ማሽኑ ከዚህ በበለጠ
መሻሻል ያለበት ብዙ ነገሮች እያሉትም ቢሆን እስካሁን ቀለል ካሉት የራስ ምታት መድሀኒቶች፣የሚጠጡ ሽሮፖችንና ሌሎችንም
ማዘጋጀት ተችሏል፡፡ ምዕራባዊያንም የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚ ለመሆን ከወዲሁ ብዙ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ክሮኒንም ሆኑ
የሞያ ባልደረባዎቹ አንድ የመደፊት ተስፋ ታይቷቸዋል፡፡ “ወደፊት ሰዎች መድሀኒቶቻቸውን በቤታቸው እንደምግብ ያዘጋጃሉ” በማለት የመደፊቱን ይተነብያል፡፡ ማን ያውቃል እንደ ክሮኒን ትንቢትም
ከምዕራባውያን አልፎ ተርፎም ወደኛ መምጣቱ አይቀር ይሆናል፡፡ሁሉንም ብቻ ጊዜ ይፈታዋል፡፡

በሁሉም
ሰው ቤት እንደሚገባ የሚጠበቀው የ3ዲ መድሀኒት ማዘጋጃ ማሽን
Comments
Post a Comment