2012 የማያ ቀን አቆጣጠር መጨረሻ ብቻ ወይስ የአለም ፍፃሜ?



-         የማያ ቀን አቆጣጠር በመጪው ዲሴምበር፣21 2012 ያበቃል
-         ይህን ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል የሚሉ ወገኖች ተበራክዋል
-         የናሳ ተመራማሪዎች ይህን ውድቅ የሚያደርግ ሪፖርት ይፋ አድርገዋል፡፡
-         የማያ ሕዝቦች የታያቸው የናሳ ተመራማሪዎች ያላዩት ምስጢር ይኖር ይሆን?
-         በእርግጥ ከምድር ጋር የምትጋጭ ድብቅ ፕላኔት ትኖር ይሁን?
-         በቅርቡ በፀሐይ ላይ የታየው ድንገተኛ ክስተት የትንቢቱ ምልክት እንደተባለው ይሆን?

        

ዘንድሮ በጉጉት ከሚጠበቁ ነገሮች መሀል የፈረንጆቹ ዲሴምበር 21 2012 ቀን ነው፡፡ የጉጉቱ ዋነኛ ምክንያትም የማያን የቀን አቆጣጠር ሰንጠረዥ ማለቅ ተከትሎ የአለም ፍፃሜ ይሆናል ተብሎ የተደረገውን ትንቢት ውጤት ምን አንደሚመስል ለማወቅ ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ብሎ ብዙ ጊዜ ሰዎች ያለም ፍፃሜ ይሆናል በማለት አሳዛኝም አስቂም ክስተቶች ተፈፅሞባቸዋል በራሳቸውም ላይ ሲፈፅሙ ታይቷል፡፡የአለም ፍፃሜን በተመለከተ ታላላቅ ቅዱስ መፃህፍትም ሆኑ ሳይንስ ከሚተነብዩት ውጭ የተደረጉ ትንቢቶችና ሙከራዎች የአለምን ሕዝብ ግራ እንዳጋቡ ቆይተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም የአለም ፍፃሜ እንደደረሰ የተነበዩ፤ እራሳቸውን ጨምሮ አያሌ ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደ ሞት ያመሩ ብዙ ግለሰቦችም ባለፉት ጥቂት አመታት ታይተዋል፡፡ ከአለማችን ቀደምት ስልጣኔዎች መሀል አንዱ የሆነው የማያ ሕዝቦች ስልጣኔ የራሱ የቀን አቆጣጠር አለው፡፡ ይህ የቀን አቆጣጠር እንዳጋጣሚ ሆኖም ይሆን ታስቦበት በመጪው የፈረንጆቹ ዲሴምበር ወር ላይ ያበቃል፡፡ ይህን ተከትሎ ማያዎች ከተነበዩት አንዳንድ ትንቢቶች በመነሳት የአለም ፍፃሜ ሊሆን እንደሚችል ብዙ ሰዎች ከወዲሁ እየተነበዩ ይገኛል፡፡

ለመሆኑ የማያ ቀን አቆጣጠር ስለአለም ፍፃሜ ይተነብያል? ለመሆኑ የዚህ ካላንደር ማለቅ የአለም ፍፃሜ ነው ማለት እንችላለን? ይህንና ሌሎች ተያያዥ ትንቢቶችን በተመለከተ የአሜሪካኑ የጠፈር ሳይንስ ተቋም ምላሽ አለኝ ይላል፡፡ ምላሹንም በዘጋቢ ፊልም ሪፖርት አድር¹ል፡፡

የናሳ ሪፖርት ምን ይላል?

የናሳው ጀት ፕሮፔልዥን ቤተሙከራ ይፋ ያደረገው ይህ ሪፖርት የፍፃሜው ሀሳብ ስህተትነትን ለማስገንዘብና እንዳንድ ግራ መጋባቶች በሕዝቦች መሀል እንዳይኖር ለማድረግ ነው፡፡ ባለፈው የፈረንጆቹ ማርች ወር ላይ የተለቀቀው ይህ ዘጋቢ ፊልም ብዙ ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን አቅርቧል፡፡ የማያ ቀን አቆጣጠር ጋር በተያያዘ ማያውያን ተነበዩት የተባለው የምፅዓት ቀን አደጋዎች ምን ያህል የተሳሳቱ እንደሆኑም መጠቆም የቻለ እንደነበር ተነግሮለታል፡፡

በናሳ ለመሬት ቅርበት ያላቸው የሕዋ አካላት ምርምር ዋና ሀላፊ ዶን ዩማንስ በዚህ ዘጋቢ ፊልም ምን ያህል የማያን ቀን አቆጣጠር ሰዎች በተሳሳተ መልኩ እንደተረጎሙት አብራርተዋል፡፡

የማያ ቀን አቆጣጠር ድንገት በዲሴምበር ወር ላይ ያበቃል፡፡ የዚህ ቀን አቆጣጠር በዚህ ወርና አመት ማለቁ የአለም ፍፃሜ ሳይሆን የአንድ ወቅት ማለቅና የአዲስ ወቅት መተካትን እንደሚያሳይ የናሳ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ “ የቀን አቆጣጠራቸው በዲሴምበር 21 2012 ቢያልቅም የአንድ ወቅት ማለቅና የአዲስ ወቅትን መተካት ስለሚያሳይ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ ማያውያን ቀጣዩን ወቅት ለምን ካላንደር አልሰሩለትም ብንል ብዙ ምክንያቶች ማንሳት እንችላለን እንጂ የአለም ፍፃሜ ሆኖ አይደለም” ያላሉ ዶን ዩማንስ
በማያ ቀን አቆጣጠር መሰረት የማያ ምፅአት ቀን የሚባለውን ጉዳይ አስመልክቶም ባለሞያው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህ በተለይ በቀጥታ የማያ ቀን አቆጣጠርን የሚያምኑና የሚከተሉ ግለሰቦች ሀሳብ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በማያ የቀን አቆጣጠር ላይ የተጠቀሱ የተፈጥሮ አደጋዎች የአለም ፍፃሜ መንስኤዎች እንደሆኑ ይናገራሉ ተመራማሪዎች ግን እነዚህ የተጠቀሱ አደጋዎች የተለመዱ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመጠቆም እንጂ የፍፃሜያችን መንስኤዎች አይደሉም ይላሉ፡፡

ሌላ ተመራማሪዎችንና የምፅአት ናፋቂዎችን ያላስማማ ጉዳይ ቢኖር የማያ ቀን አቆጣጠር በሚያልቅበት ወቅት ከምድር ጋር የምትጋጭ ኒቡሩ የምትባል ፕላኔት አለች የሚለው ትንቢት ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ደግሞ “ይህች ፕላኔት በዲሴምበር 21 እለት ከምድር ጋር የምትጋጭ ከሆነ ቢያንስ በአሁን ሰዓት በቅርበት መታየት ትችል ነበር፡፡” ይላሉ ዶን ዩማንስ የተጠቀሰችው ፕላኔት ሀሳባዊ እንደሆነች ለማስረዳት፡፡
    

የናሳው ቃል አቀባይ ዶን ዩማንስ

ፕላኔቷ የታለች?

“ፕላኔቷ የታለች?” በማለት ይጠይቃሉ የናሳው ባለስልጣን ዩማንስ “እውነት ለመናገር ይህች የተጠቀሰችው ፕላኔት ከመሬት ጋር ለመጋጨት ካቀደች ቢያንስ በቅርበት መገኘት አለባት፡፡” በማለት የኒቡሩ ፕላኔት ሀሳባዊ ፈጠራ እንጂ እንደሌለች ያስረዳሉ፡፡ ሌላኛው የናሳ ተመራማሪ እንደሚስረዱት ቢያንስ ይህች ፕላኔት ባናያት እንኳን አለች ከተባለ የስበት ሀይል በሁለቱ ፕላኔቶች መሀል ሊፈጠር እንደሚችል እና በቀላሉ ሊለይ እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ አልያ ግን ህች ፕላኔት ብትኖርና ለእይታ የራቀች ከሆነች ቢያንስ ምድር ጋር ለመድረስ ሌሎች አመታትንና የዲሴምበር ወርን እንጠብቅ በማለት ተመራማሪዎቹ በሃሳቡ ተሳልቀዋል፡፡

በአጠቃላይ የተባለችውም ፕላኔት እስካሁን አልታየችም፡፡ በተባለው መሰረትም ይታያሉ የተባሉት አሰቃቂ ቅድመ የተፈጥሮ አደጋዎችም እንደተባለው ሳይሆን ባልተባለው መልኩ ወይም ሳከሰቱ አልፈዋል፡፡
ዩማንስ እንደሚያጠቃልለውም “ከናሳ ሽፋን የማምለጥ እድሏ ዜሮ ነው፡፡ ይህች ፕላኔት ብትኖር ሕዋውን በየቀኑ የሚስሱ አስትሮኖመሮች ያገኛት ነበር፡፡” ይላሉ እናም የኒቡሩ ፕላኔት ሀሳባዊ እንጂ በእውነተኛው አለም እንደሌለች የሁሉም ተመራማሪ እምነት ነው፡፡

ሌላኛው የምፅዓት ምልክት?

የማያን ቀን አቆጣጠር በማስታከክ የአለም ፍፃሜ ሀሳብ የሚያራግቡም ግለሰቦችም ሆነ ይህን ለግል ጥቅም ለሚያውሉ ግለሰቦች ሌላኛው የመከራከሪያ ነጥባቸው እየታየ ያለው የተፈጥሮ አደጋ እና በቅርብ ቀናት በፀሀይ ላይ የተከሰተው ድንገተኛ ክስተት በማያ ቀን አቆጣጠር ውስጥ የተጠቀሱትን አደጋዎች ስለሚመስል እንደሆነ በመጠቆም ነው፡፡

ይህን በተመለከተም ናሳ አግባብ ያለው መልስ አለኝ ይላል፡፡ እንደ ናሳ ባለሞያዎች እምነትም በቅርብ ጊዜ በፀሀይ ዙሪያ የተከሰተው ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ጨረር ፈንጥቆ ወደ ሕዋው በፍንዳታ መልክ መሰራጨቱ የምድር ምፅዓት መምጣቱ ሳይሆን ሌላ ተፈጥ[ዊ ሒደት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይህ ተፈጥ[ዊ ሒደት ፀሐይ በየ11 አመታት አንድ ጊዜ የምታርገው ሒደት ነው እናም ከዚህ ፊት የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል  እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ሌላኛው የምፅዓት ቀን ናፋቂዎች መከራከሪያ ነጥብ የፕላኔቶች የምህዋር መገጣጠምና የእርስ በእርስ ግጭት ሊኖር ይችላል የሚል ግምት ነው፡፡ ዩማንስም ይህን በተመለከተ እንደሚናገሩት አንዳንድ የምፅዓት ናፋቂዎች ምድራችን ምህዋ[ን በመሳት ከሌሎች ፕላኔቶች ጋር ምንም አይነት የመጋጨት አደጋ አይከሰትም፡፡ ምድራችን ከምህዋ[ፈቀቅ ብትል እንካን የግጭት አደጋው የሚያሰጋት ከጨረቃ እና ከፀሐይ ጋር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሊከሰት አይችልም ምክንያቱም በነዚህ አካላት መሀል ርቀቱንና ቋሚነቱን የሚስጠብቅ የሞገድ ሀይል አለ፡፡ ስለዚህ ይህም የማይታሰብ ነው በማት መላምቶቹን ውድቅ ያደርጋሉ፡፡

መጪው ቀን ዲሴምበር 21 2012

  በእርግጥ በዚች ቀን ምን እንጠብቅ? የምፅዓት ናፋቂዎችን መላምት ወይም የናሳ ተመራማሪዎችን ድምዳሜ? እንደ እውነቱ ከሆነ ከጥቂት ግለሰቦችና ማሕበረሶች በስተቀር አለም ጉዳዩ ያሰጋው አይመስልም፡፡ በተመራማሪዎች ዘንድም ስጋት ውስጥ የከተተና ፈታኝ የሆኑ ምክንያቶችን እንደሌሉ ይናገራሉ፡፡

እንደዩማንስ ያሉ የናሳ ተመራማሪች እንደሚናገሩትም መጪዋ የፈረንጆቹ ዲሴምበር ወር እለተ ቀን 21 ከሌሎቹ ቀናት የማትለይና የተለመደች ቀን እንደምትሆን አይጠራጠሩም እኛስ ምን እንገምታለን? ምንስ እንጠብቅ? የማንኛቸውስ ትክክልና አሳማኝ መስሎ ታይቶን ይሆን?

ይህንንም ጊዜ ይፈታው ዘንድ ወደድን፡፡ እኛም የሚሆነውን ለማየት ያበቃን ዘንድ  እስከ ዲሴምበር 21 2012 ብቻም ሳይሆን ከዛም በላይ ያቆየን ዘንድ ምኞታችን ነው፡፡

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ቪያግራም እንደ ራስ ምታት ክኒን?

ብቸኝነትና ግለኝነት የዘመኑ ወረርሽኝና ሰለባዎቹስ እነማን ናቸው?

ራሰ በራበት እንዴት ሊቀር ይችላል? የራሰ በራነት መድሐኒቶችስ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?